Home Learn EnglishLearn English የታዋቂው ቅርጫት ኳስ ተጫዋች ማይክል ጆርዳን ጫማ በ23 ሚሊዮን ብር በጨረታ ተሸጠ

የታዋቂው ቅርጫት ኳስ ተጫዋች ማይክል ጆርዳን ጫማ በ23 ሚሊዮን ብር በጨረታ ተሸጠ

by sam

በዚህ ሳምንት በበይነ መረብ በነበረው ጨረታ ላይ ናይክ ጆርዳን 1 የተባለው የስፖርተኛው ጫማ መሸጡም ተገልጿል። ጫማውም በቺካጎ ቡልስ ቡድን ይጫወት በነበረበት ወቅት በጎርጎሳውያኑ 1985 ያጠለቀው ነው ተብሏል። በዚህ ጫማም ወደላይ በመዝለል በርካታ ኳሶችን በመረቡ በማስቆጠርም በታሪካዊነቱ የተመዘገበ ነው። በርካታ ስፖርታዊና የስነጥበብ ጨረታዎችን በማካሄድ የሚታወቀው ክርስቲስ የተባለው ኩባንያ እስካሁን ድረስ ዘጠኝ የማይክል ጆርዳን ጫማዎችን ሸጧል። እነዚህ ጫማዎችም ማይክል ጆርዳን ለአስራ አራት አመታት የነገሰበትን የቺካጎ ቡልስ ቡድን ቆይታውን ለመዘከርም ነው።

Leave a Comment

Related Posts

en_USEnglish