Home Learn EnglishLearn English ጃፓናዊው ቢሊየነር ወደ ጨረቃ አብራችሁኝ መጓዝ የምትፈልጉ ማመልከቻ አስገቡ አለ

ጃፓናዊው ቢሊየነር ወደ ጨረቃ አብራችሁኝ መጓዝ የምትፈልጉ ማመልከቻ አስገቡ አለ

by sam

ጃፓናዊው ቢሊየነር  ወደ ጨረቃ አብረውኝ የሚጓዙ ስምንት ሰዎችን እፈልጋለሁ አለ

ያሳኩ ማኢዛዋ ወደ ጨረቃ የሚጓዘው በአሜሪካዊው ቢሊየነር ኤለን ማስክ ድርጅት በሚዘጋጀው የሕዋ ጉዞ ነው።

”ከተለያየ የማህብረሰብ ክፍል የሚመጡ ሰዎችን ነው የምፈልገው” ብሏል በትዊተር ገጹ ላይ ባስተላለፈው የተንቀሳቃሽ ምስል መልዕክት። ቢሊየነሩ ወደ ጨረቃ ለመሄድ የሚፈልጉ ሰዎች ሊያመለክቱ የሚችሉበትን የድረ-ገጽ አድራሻም አስቀምጧል።

ፍቃደኝነታቸውን በመግለጽ ወደ ጨረቃ ለመሄድ የሚመረጡ ሰዎች ወደ ጨረቃ ለሚደረገው ጉዞ ሙሉ ወጪያቸው እንደሚሸፈን ቢሊየነሩ አስታውቋል።

Leave a Comment

Related Posts

en_USEnglish