Home Entertainment News ባለ 14 ካራት ትንሽዬ አልማዝ በ26 ሚሊዮን ዶላር ተሸጠች

ባለ 14 ካራት ትንሽዬ አልማዝ በ26 ሚሊዮን ዶላር ተሸጠች

by sam

ለማግኘት በጣም ከባድና ውድ የተባለ አንድ ሐምራዊ አልማዝ ክብረ ወሰን በሚባል ዋጋ ተሸጠ። ይህ አልማዝ የተሸጠው በጨረታ ሲሆን ጨረታው ስዊዘርላንድ አገር ነው የተካሄደው።

14.8 ካራት የሚመዝነው ይህ አልማዝ “ዘ ስፕሪት ኦፍ ሮዝ” የሚል ስም ተሰጥቶታል። እስከዛሬም ለጨረታ ከቀረቡ አልማዞች ትልቁ ነው።

99 ከመቶ የሚሆኑ የሐምራዊ ሮዛማ ቅይጥ ቀለም ያላቸው አልማዞች የካራት መጠን ከ10 በታች እንጂ 14 ካራት አይደርሱም።ይህን አልማዝ ልዩ የሚያደርገውም መጠኑና የቀለም ስብጥሩ ነው ተብሏል።ይህን ውድ አልማዝ በጨረታ አሸንፎ የገዛው ግለሰብ ማንነት ይፋ አልተደረገም።

Leave a Comment

Related Posts

en_USEnglish