Home Entertainment News የአማዞን ደን በ12 አመት ውስጥ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ መጨፍጨፉ ተነገረ

የአማዞን ደን በ12 አመት ውስጥ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ መጨፍጨፉ ተነገረ

by sam

የአለም ሳምባ እንደሆነ የሚታመነው የአማዞን ደን በ12 አመት ውስጥ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ መጨፍጨፉ ተነግሯል።

በብራዚሉ የአማዞን ደን ላይ የሚካሄደው ጭፍጨፋና እ.ኤ.አ ከ2008 ወዲህ እየተባበሰ መምጣቱን የአገሪቱ ስፔስ ኤጀንሲ አስታውቋል።

በተባባሰው የደን ጭፍጨፋ እ.ኤ.አ ከነሐሴ 2019 እስከ ሰኔ 2020 ብቻ ከ11 ሺህ ስኩዌር ኪሎሜትር በላይ የሚሆነው የአማዞን ደን ክፍል መጨፍጨፉ ተገልጿል።

ይህም ባለፉት ዓመታት በደኑ ላይ ከተደረጉ ጭፍጨፋዎች 9 ነጥብ 5 በመቶ ጭማሬ ማሳየቱንና ከ12 ዓመታት ወዲህም ከፍተኛው የደን ጭፍጨፋ መካሄዱን እንዳሳየ ቢቢሲ ዘግቧል።

አማዞን የዓለምን የሙቀት መጨመር ፍጥነት የሚቀንስ ወሳኝ የካርቦን ክምችት ያለው መሆኑ እየታወቀ የብራዚል ፕሬዚዳንት ጄይር ቦልሴናሮ በደኑ ላይ ምንጠራና እርሻ ይስፋፋ ሲሉ ማበረታተቸው አስወቅሷቸዋል።

የዘርፉ ተመራማሪዎችም የብራዚል መንግስት ጉዳዩን ትኩረት ሰጥቶ እንዲያስብበት አጽንኦት ሰጥተዋል።

በሌላ በኩል ብራዚል በደኑ ላይ የሚደረገውን ጭፍጨፋ በየአመቱ ወደ 3 ሺህ 900 ስኩዌር ኪሎ ሜትር ለመቀነስ ማቀዷን ገልጻለች ተብሏል።

የአማዞን ደን ለተለያዩ አገልግሎቶች በየአመቱ በከፍተኛ ሁኔታ የሚመነጠር ሲሆን ከዚህም ውስጥ ለፋብሪካ ግብዓት፣ ለቤት ግንባታ፣ ለአላቂ ምርቶችና ለእርሻ አገልግሎት በደኑ ላይ ምንጠራ ይካሄዳል።

የአማዞን ደን ሶስት ሚሊዮን ገደማ ለሚሆኑ ህጽዋትና እንስሳት ዝርያዎች መኖሪያ ሲሆን አንድ ሚሊዮን የሚጠጉ ነባር ህዝቦች ደግሞ የሚኖሩበት ሰፊ ብዝሃ ህይወት ያለው ነው።

Leave a Comment

Related Posts

en_USEnglish