Home Entertainment News አሜሪካዊው ራፐርና ፕሮዲዩሰር ዶ/ር ድሬ ሆስፒታል ገባ

አሜሪካዊው ራፐርና ፕሮዲዩሰር ዶ/ር ድሬ ሆስፒታል ገባ

by sam

በሙዚቃው ኢንዱስትሪ ውስጥ ስኬታማ እና ተደማጭነት ካላቸው አሜሪካውያን መካከል አንዱ የሆነው ራፐር እና ፕሮዲዩሰር ዶ/ር ድሬ በአንጎል የደም ቧንቧ ችግር ምክንያት በሆስፒታል ህክምና እየተደረገለት ይገኛል፡፡

የ55 ዓመቱ ዶ/ር ድሬ ሎስ አንጀለስ ወደ ሚገኘው ሴዳርስ-ሲናይ ህክምና ማዕከል ተወስዷል ሲል ቲኤምዚ ዘግቧል፡፡

ዶ/ር ድሬም በኢንስታግራም ገጹ ላይ ባሰፈረው ጽሑፍ ላይ “ጥሩ እያገገምኩ እና በህክምና ቡድኔ ጥሩ እንክብካቤ እያገኘሁ ነው” ብሏል፡፡

ከበሽታው በኋላ “እረፍት እያደረገ ነው” ሲሉ ጠበቃው ለቢልቦርድ ተናግረዋል፡፡

“ከሆስፒታል ወጥቼ በቅርቡ ወደ ቤቴ እመለሳለሁ፡፡ በሴዳር ለሚገኙ ታላላቅ የህክምና ባለሙያዎች ምስጋና አቅርቡልኝ፡፡ አንድ ፍቅር” ሲል ዶ/ር ድሬ ያለበትን አካፍሏል።

የጤንነቱ ሁኔታ ከተገለጸ በኋላ ጓደኞቹ እና ባልደረቦቹ መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡

Leave a Comment

Related Posts

en_USEnglish