Home Entertainment News አንጋፋው የቴሌቪዥን አቅራቢ ላሪ ኪንግ በ87 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

አንጋፋው የቴሌቪዥን አቅራቢ ላሪ ኪንግ በ87 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

by sam

 አንጋፋው የአሜሪካ የቴሌቪዥን አቅራቢ ላሪ ኪንግ በ87 ዓመቱ ሕይወቱ ማለፉ ተገለጸ። 

ከ60 ዓመታት በላይ በሚዲያው ላይ የቆየው ላሪ ኪንግ በተለይ ለ25 ዓመታት በሲኤንኤን ቴሌቪዥን ሲያዘጋጅ በቆየው የራሱ ፕሮግራም ይታወቅ ነበር። 

በዚህ ፕሮግራሙ ለበርካታ ትላልቅ መሪዎች፣ ዝነኛ ሰዎች እና ታዋቂ አትሌቶች ቃለ-መጠይቅ አድርጓል። 

ለረጅም ዓመታት በቆየበት ሙያው በርካታ ሽልማቶች እና እውቅናዎችን ያገኘው ላሪ ኪንግ በኮቪድ-19 ተይዞ ሆስፒታል የገባው ባለፈው ወር እንደነበር ቢቢሲ ዘግቧል። 

Leave a Comment

Related Posts

en_USEnglish