Home Entertainment News ግብጽ ከወርቅ የተሠራ ምላስ የተገጠመላቸው 2ሺህ ዓመታት ያስቆጠሩ አፅሞችን አገኘች

ግብጽ ከወርቅ የተሠራ ምላስ የተገጠመላቸው 2ሺህ ዓመታት ያስቆጠሩ አፅሞችን አገኘች

by sam

የግብጽ በመሬት ውስጥ የተቀበሩ ቅርሶች ጥናት ተመራማሪዎች 2ሺ ዓመት ያስቆጠሩ አፅሞችን አገኙ፡፡

አፅሞቹ ወደ አፈርነት እንዳይቀየሩ በመድኃኒት አድርቆ የማቆየት ጥበብ የተጠበቁ ሲሆን ልዩ የሚያደርጋቸው ግን ምላሳቸው በወርቅ መተካቱ ነው፡፡

የግብጽና የዶሚኒካን ቡድን በአሌክሳንድሪያ ከተማ፣ በታፖሲሪስ ማግና ቤተ መቅደስ አካባቢ 16 በማድረቂያ የተጠበቁ አፅሞችን ከአለት በተሰሩ የመቃብር ቤቶች ውስጥ እንዳሉ ነው ያገኙት፡፡

ከፍ ባለ እርከን ላይ የሚገኙ ሰዎችን በዚህ መንገድ አንዳንድ የሰውነት ክፍላቸውን በወርቅ ተክቶ መቅበር በግሪክና ሮማዊያን ሥልጣኔ ዘመን የተለመደ ነበር፡፡

ምናልባት አፅሞቹ ምላሳቸው በወርቅ የተሰራላቸው ከሞት በኋላ ይኖራል ብለው በሚያምኑት ሕይወት የፍርድ ቀን ላይ ጣኦት ኦሲሪስን አቀላጥፈው እንዲያናግሩት ያግዛቸዋል በሚል እንደሆነ ተገምቷል፡፡

Leave a Comment

Related Posts

en_USEnglish