Home Entertainment News ቢዮንሴ እና ቴይለር ስዊፍት በ2021 የግራሚ ሽልማት ላይ ታሪክ ሰሩ

ቢዮንሴ እና ቴይለር ስዊፍት በ2021 የግራሚ ሽልማት ላይ ታሪክ ሰሩ

by sam

ቢዮንሴ ለ28ኛ ጊዜ የግራሚ ሽልማትን በማግኘት እንዲሁም ቴይለር ስዊፍት ለሦስት ተከታታይ ዓመታት የዓመቱ ምርጥ አልበም ሽልማትን በመውሰድ ታሪክ አስመዘገቡ።

በአሁኑ ጊዜ ቢዮንሴ በግራሚ ሽልማት ታሪክ ከፍተኛ ቁጥር ያለውን ሽልማት ያሸነፈች ሴት ድምጻዊት በመሆን ቀዳሚነቱን ይዛለች።

ከዚህ ቀደም ይህንን ክብረወሰን ጨብጣ የነበረችው አሊሰን ክራውስ ነበረች።

63ኛው የግራሚ ሽልማት በሎስ አንጀለስ የተካሄደ ሲሆን በተለምዶ “የሙዚቃ ትልቁ ምሽት” በመባል ይታወቃል።

በዚህ ዓመት በኮሮናቫይረስ ወርሽኝ የተነሳ ከዚህ ቀደም ከነበሩት የሽልማት ሥነ ሥርዓቶች በተለየ ምንም ዓይነት እንግዳ ሳይገኝ ዝግጅቱ ተካሂዷል።

ቢዮንሴ በምርጥ የአር ኤንድ ቢ ሙዚቃ አቀራረብ ተመርጣ ሽልማቱን ስትቀበል “ታላቅ ክብርና ደስታ ይሰማኛል” ብላለች።

ቴይለር ስዊፍትም እንዲሁ ሦስት ግዜ የዓመቱ ምርጥ አልበምን በማሸነፍ የመጀመሪያዋ ሴት በመሆን ታሪክ ሰርታለች።

ድምጻዊቷ ሽልማቱን ያገኘችው በኮሮናቫይረስ ውሸባ ውስጥ ሆና በሰራችውና “ፎክሎር” የሚል መጠሪያ በሰጠችው አልበሟ ነው።

Leave a Comment

Related Posts

en_USEnglish