Home Entertainment News የልዕልት ዲያና ደብዳቤዎች ለጨረታ ሊቀርቡ ነው

የልዕልት ዲያና ደብዳቤዎች ለጨረታ ሊቀርቡ ነው

by sam

የዌልስ ልዕልት በነበረችው ዲያና በእጅ የተፃፉ ደብዳቤዎች ከሰሞኑ በእንግሊዙ ለጨረታ ሊቀርቡ ነው።

የጨረታ አቅራቢው ኮርንዋል እንዳስታወቀው አርባ ደብዳቤዎችንና የሰላምታ ካርዶችንም አዘጋጅቷል።

ደብዳቤዎቹ በአውሮፓውያኑ 1990-1997 የተፃፉ ሲሆኑ፤ ለጓደኛዋ ሮጀር ብራምብል የተፃፉ ደብዳቤዎች ተካትተውበታል ተብሏል።

በአውሮፓውያኑ ሰኔ 12 1992 ተፃፈ በተባለ ደብደቤ “አስፈሪ ሳምንት” ነው ስትል ገልፃ ነበር።

በወቅቱም አንድሪው ሞርተን የተባለ ጋዜጠኛ የልዕልቲቱን ህይወት ታሪክ ያሳተመበት ወቅት ሲሆን የመፅሃፉ ታሪክም በሰንደይ ታይምስ እየተቀነጨበ እየቀረበ ነበር። ደብዳቤዎቹ ከ300 ፓውንድ-1500 ፓውንድ ዋጋ ተተምኖላቸዋል።

Leave a Comment

Related Posts

en_USEnglish