Home Entertainment News የቢል ጌትስን፣ የኦባማንና የኤለን መስክን ትዊተር ገጽ የመነተፈው ወጣት ተፈረደበት

የቢል ጌትስን፣ የኦባማንና የኤለን መስክን ትዊተር ገጽ የመነተፈው ወጣት ተፈረደበት

by sam

አሜሪካዊው የ17 ዓመት ወጣት የሥመ ጥር ሰዎችን የትዊተር ገጽ ሰርስሮ በመግባት የማጭበርበር ወንጀል በመፈጸሙ ጥፋተኛ ተባለ፡፡

ወጣቱ ግራሐም ኢቫን ክላርክ ይባላል፡፡ ይህንን ወንጀል ሲፈጽም እድሜው 17 ነበር፡፡ አሁን 18ኛ ዓመቱን ይዟል፡፡

ወጣቱ ከቢትኮይን የዲጂታል ገንዘብ ጋር በተያያዘ ነው የማጭበርበር ወንጀሉን የፈጸመው፡፡

መጀመርያ የሥመጥርና ገናና ሰዎችን የትዊተር አካውንቶች በመጥለፍና ሰርስሮ በመግባት ገንዘብ ለማሰባሰብ ሞክሯል፡፡

የትዊተር ገጻቸው በወጣቱ ከተመነተፈባቸው ሥመጥሮች መካከል የቲቪ ዝነኞች ቁንጮ ኪም ካርዳሺያን ዌስት፣ ቢሊየነሮቹ ኤለን መስክና ቢልጌትስ፣ እንዲሁም የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ ይገኙበታል፡፡

ይህ ወጣት ምንተፋውን ካቀነባበረ በኋላ በዝነኞቹ የትዊተር ገጽ ላይ ተከታዮቻቸው ገንዘብ እንዲረዱ የሚጠይቅ ጽሑፍ ለጥፏል፡፡

ለምሳሌ የቢሊየነሩን ቢልጌትስ አካውንት ሰርስሮ ከገባ በኋላ እንዲህ ሲል ሐሰተኛ መልእክት አስተላልፏል፡፡

‹‹ሰዎች ከሐብቴ እየቀነስኩ በቢትኮይን ለኮቪድ ተጠቂዎች እርዳታ እንዳደርግ ጠይቀውኛል፡፡ እነሆ እናንተ 1ሺ ዶላር ስትልኩልኝ እኔ በአድራሻችሁ 2ሺ ዶላር እልካለሁ››

በዚህ ሐሳዊ ዘዴ ወጣቱ 117ሺ ዶላር የሚገመት የክሪፕቶከረንሲ ገንዘብ መመንተፍ ችሏል፡፡

ወጣቱ በቁጥጥር ሥር ከዋለ በኋላ ግን ያጭበረበረውን ገንዘብ በማመኑ ገንዘቡ ወደተመዘበረባቸው ሰዎች እንዲመለስ ሆኗል፡፡

የ17 ዓመቱ ወጣት አሁን በፍሎሪካ ፍርድ ቤት ለ3 ዓመት ዘብጥይ እንዲወርድ ተወስኖበታል፡፡

ከዚህ በኋላም ኮምፒውተር ሲጠቀም ከተቆጣጣሪ/ከጸጥታ ኃይሎች ጋር እንጂ ብቻውን ድርሽ እንዳይል ፍርድ ቤቱ በይኗል፡፡

Leave a Comment

Related Posts

en_USEnglish