Home Entertainment News የጃክ ዶርዚ የመጀመሪያ ትዊት በ2.9 ሚሊዮን ዶላር [117 ሚሊዮን ብር ገደማ] ተሸጠ።

የጃክ ዶርዚ የመጀመሪያ ትዊት በ2.9 ሚሊዮን ዶላር [117 ሚሊዮን ብር ገደማ] ተሸጠ።

by sam

ትዊተር የተሰኘው ማሕበራዊ ድር አምባ ፈጣሪ የሆነው ጃክ ዶርዚ የመጀመሪያ ትዊት በ2.9 ሚሊዮን ዶላር [117 ሚሊዮን ብር ገደማ] ተሸጠ።

ትዊቱን የገዛው ማሌዢያ ውስጥ የሚገኝ አንድ ሃብታም እንደሆነ ተጠቁሟል።

የመጀመሪያው መልዕክት “ትዊተሬን እያዘጋጀሁ እገኛለሁ” የሚል ሲሆን የተለጠፈው በፈረንጆቹ መጋቢት 21/2006 ነበር።

ዶርዚ ይህንን ትዊት ለጨረታ ያቀረበው ገቢውን ለእርዳታ ለማዋል በማሰብ ነው።

መቀመጫውን ማሌዢያ ያደረገው ገዥ ሲና ኤስታቪ ትዊቱን መግዛት ማለት የሞና ሊዛን ስዕል እንደመግዛት ነው ብሏል

Leave a Comment

Related Posts

en_USEnglish