Home Entertainment News በ10 ሳንቲም ሲሸጥ የነበረ መጽሔት ከ3 ሚሊዮን ዶላር በላይ አወጣ

በ10 ሳንቲም ሲሸጥ የነበረ መጽሔት ከ3 ሚሊዮን ዶላር በላይ አወጣ

by sam

ቆየት ያለው የቀልድ ይዘት ያለው እና ሱፐር ማንን ያስተዋወቀ ነው የተባለው ህትመት ክብረ ወሰን በሆነ ዋጋ ነው ተሸጠ።

በ3.25 ሚሊዮን ዶላር [ከ130 ሚሊዮን ብር በላይ] የተሸጠው ይህ አስቂኝ ይዘት ያለው መጽሔት ከመደበኛ ሰው የላቀ ኃይል ያለው ገፀባህሪን (ሱፐርማን) ለመጀመሪያ ጊዜ ያስተዋወቀ ነው ተብሏል።

ታዲያ የመገኘት ዕድሉ ጠባብ እንደሆነ የተነገረለት ይህ ዕትም የተሸጠበት ዋጋ ክብረ ወሰን ነው።

‘አክሽን ኮሚክ’ ቁጥር 1 የሚል ርዕስ ያለው ህትመቱ፣ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1938 ሲወጣ የመሸጫ ዋጋው 10 ሳንቲም ነበር። ታዲያ አሁን ላይ የተሸጠበት ዋጋ መጽሔቱን በዓለም ውዱ ቀልድ አዘል ህትመት አድርጎታል።

የሱፐር ማንን አነሳስ የሚያትተው ህትመቱ የዚህ ዓይነት ዘውግን ለመጀመሪያ ጊዜ ያስተዋወቀ እንደሆነ ይታመናል።

አሁን ላይ የ ‘አክሽን ኮሚክ’ ቁጥር 1 ህትመት 100 የሚሆኑ ዕትሞች እንዳሉ ይገመታል።

Leave a Comment

Related Posts

en_USEnglish