Home Entertainment News አሜሪካዊው ራፐርና የፊልም ተዋናይ ዲኤምኤክስ አረፈ

አሜሪካዊው ራፐርና የፊልም ተዋናይ ዲኤምኤክስ አረፈ

by sam

አሜሪካዊው የራፕ ሙዚቃ አቀንቃኝና የፊልም ተዋናይ ዲኤምኤክስ ለአምስት ቀናት በልብ ህመም ህክምና ላይ ከቆየ በበኋላ በ50 ዓመቱ አረፈ።

በትክክለኛ ስሙ ኧርል ሲሞንስ በሚል የሚታወቀው ዲኤምኤክስ ሆስፒታል ውስጥ ቤተሰቦቹ ባሉበት በስትንፋስ ማቆያ መሳሪያ ሲረዳ ቢቆይም ህይወቱ አልፏል።

ቤተሰቡ ከህልፈቱ በኋላ ባወጣው መግለጫ ዲኤምኤክስ “አስከመጨረሻው ድረስ የተፋለመ ጠንካራ ነበር” ብሏል።

“ሙዚቃው በመላው ዓለም ያሉ ለቁጥር የሚታክቱ አድናቂዎቹን ያነቃቃ ሲሆን ጥሎት ያለፈው የተለየው ውርስም ለዘላለሙ ይኖራል” ሲል ጨምረዋል።

የ15 ልጆች አባት የሆነው ዲኤምኤክስ እንስሳት ላይ ጭካኔ የተመላበት ድርጊት በመፈፀም፣ በግዴለሽነት በማሽከርከር፣ እንዲሁም አደንዛዥ እፅ እና የጦር መሳሪያ ይዞ በመገኘት እስር ቤት ገብቶ ያውቃል።

እንደ ቤተሰቡ ከሆነ ዲኤምኤክስ የሞተው አርብ ዕለት ኒው ዮርክ ዋይት ፕሌንስ ውስጥ በሚገኘው በዋይት ፕሌይንስ ሆስፒታል ነው።

Leave a Comment

Related Posts

en_USEnglish