Home Entertainment News ማሊያዊቷ እናት በአንድ ጊዜ 9 ልጆችን ተገላገለች

ማሊያዊቷ እናት በአንድ ጊዜ 9 ልጆችን ተገላገለች

by sam

የማሊ ዜግነት ያላት እናት በአንድ ጊዜ ዘጠኝ ልጆችን መገላገሏ ተሰምቷል፡፡

ሃሊማ ሲሼ የ25 ዓመት ወጣት ማሊያዊ ስትሆን፤ በሞሮኮ ሃገር ሆስፒታል ዘጠኝ ልጆችን መገላገሏን የማሊ ጤና ሚኒስቴር ገልጿል፡፡ 

ወጣቷ 7 ልጆችን እንደምትወልድ በአልትራሳውንድ መመርመሪያ ታይቶ ስትጠበቅ የነበረ ቢሆንም፤ አምስት ሴቶችና አራት ወንዶችን በሰላም መገላገል እንደቻለች ተነግሯል፡፡

በአሁኑ ወቅትም እናት እና የተወለዱት ልጆች በሙሉ ጤና ላይ እንደሚገኙም ዶክተር ሲቤ የገለጹ ሲሆን፤ ከጥቂት ሳምንታት በኋላም ከሆስፒታል ይወጣሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተናግረዋል፡፡

Leave a Comment

Related Posts

en_USEnglish