Home Entertainment News የቻይናን እገዳ ተከትሎ የቢትኮይን ዋጋ በከፍተኛ ደረጃ አሽቆለቆለ

የቻይናን እገዳ ተከትሎ የቢትኮይን ዋጋ በከፍተኛ ደረጃ አሽቆለቆለ

by sam

ቻይና በክሪፕቶከረንሲ ላይ የጣለችውን እገዳ ተከትሎ የአንድ ቢትኮይን ዋጋ ከ34 ሺህ ዶላር በታች አሸቆለቆለ።

የቢትኮይን ዋጋው በዚህ ደረጃ ሲያሽቆለቁል ከሦስት ወራት በኋላ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።

ቤጂንግ ማክሰኞ ዕለት የገንዘብ ተቋማት እና የክፍያ ኩባንያዎች ከክሪፕቶከረንሲ ግብይቶች ጋር የተያያዙ አገልግሎቶችን እንዳይሰጡ አግዳለች።

ቻይና ባለሃብቶችንም በክሪፕቶከረንሲ ከሚያደርጉት የንግድ እንቅስቃሴ እራሳቸውን እንዲቆጥቡ አሳስባለች።

ክሪፕቶከረንሲን ዲጂታል መገበያያ ገንዘብ ብለን በግርድፉ ልንጠራው እንችላለን። ቢትኮይን ደግሞ በስፋት ተቀባይነት ካገኙት ዲጂታል ገንዘቦች መካከል አንዱ ነው

ከቀናት በፊት የኤሌክትሪክ መኪና አምራቹ ቴስላ ለማመርታቸው መኪኖች ቢትኮይንን በክፍያ መልክ አልቀበልም ማለቱን ተከትሎ የቢትኮይን ዋጋ 10 በመቶ ቀንሶ ነበር።

ሰኞ ዕለት ደግሞ የክሪፕቶከረንሲው ዋጋ በ22 በመቶ ቀንሷል። ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ ብቻ 6 ሺህ ዶላር ገደማ ዋጋውን ወርዷል።

እንደ ኢተርዩም እና ዶጅኮይን ያሉ ሌሎች ዲጂታል ገንዘቦች ደግሞ በቅደም ተከተል የ 25 በመቶ እና 29 በመቶ ቅናሽ አስመዝግበዋል።

በተመሳሳይ ወቅት የቴስላ አክሲዮን በዎል ስትሪት ያለው ዋጋ ከሦስት በመቶ በላይ የቀነሰ ሲሆን የኤሌክትሪክ መኪና አምራቹ ከቢትኮይን ጋር በመያያዙ ሊሆን ይችላል ተብሏል።

በኤሎን መስክ ባለቤትነት የተያዘው ኩባንያ እስከ 1.5 ቢሊዮን ዶላር የሚሆን ክሪፕቶከረንሲ በእጁ ይገኛል።

Leave a Comment

Related Posts

en_USEnglish