Home Entertainment News ሙሽሮቹ ኮቪድን ሽሽት ሰማይ ላይ ድል ያለ ሠርግ ደገሱ

ሙሽሮቹ ኮቪድን ሽሽት ሰማይ ላይ ድል ያለ ሠርግ ደገሱ

by sam

ሕንዳዊያን ሙሽሮች ቻርተርድ አውሮፕላን ተጠቅመው በሰማይ ላይ ድል ያለ ሠርግ ደግሰው መነጋገርያ ሆነዋል፡፡

በዚህ የሰማይ ላይ የሠርግ ሥነ ሥርዓት 160 እንግዶች ተጠርተው በልተው፣ ጠጥተው ጨፍረው ተበትነዋል ተብሏል፡፡

ሙሽሮቹ ሠርጋቸውን በሰማይ ለማድረግ የተገደዱት በሕንድ ኮሮና ወረርሽኝ በመዛመቱ ይህን ተከትሎ የወጣው ጥብቅ የእንቅስቃሴ ገደቡ ሊያፈናፍናቸው ባለመቻሉ ነው፡፡

በማኅበራዊ የትስስር ገጾች በአያሌው በተጋራው የሠርግ ድግስ ምሥል ላይ እንደታየው እንግዶች በቻርተርድ አውሮፕላን ውስጥ በተጨናነቀ ሁኔታ ሲስተናገዱ ነበር፡፡

ሙሽሮቹ ከሕንድ የታሚል ናዱ ግዛት የመጡ ናቸው፡፡ ቻርተርድ አውሮፕላኑም የተነሳው ከዚያው ነው፡፡

ታሚል ናዱ ግዛት የእንቅስቃሴ ገደቦችን የጣለች ሲሆን ማንኛውም የሕዝብ ስብስብ ከ50 ሰው እንዳይበልጥ የሚያስገደድ ደንብ አውጥታ እንደነበር ይታወሳል

Leave a Comment

Related Posts

en_USEnglish