Home Entertainment News አንጀሊና ጆሊና ብራድ ፒት በጋራ ልጆቻቸውን እንዲያሳድጉ ተወሰነ

አንጀሊና ጆሊና ብራድ ፒት በጋራ ልጆቻቸውን እንዲያሳድጉ ተወሰነ

by sam

ከረዥም ጊዜ እልህ አስጨራሽ የፍርድ ክርክር በኋላ ብራድ ፒት ከአንጀሊና ጆሊ ጋር ልጆቻቸውን በጋራ እንዲያሳድጉ ተወስኖለታል።

ታዋቂዋ አሜሪካዊት ተዋናይት ፍቺ የጠየቀችው በአውሮፓውያኑ 2016 ሲሆን ከዚያም በኋላ ጉዳዩን ፍርድ ቤት ይዞት ነበር።

አሁን ፍርድ ቤቱ ባሳለፈው ውሳኔ መሰረት ብራድ ፒት ከልጆቹ ጋር የሚያሳልፈውን ጊዜ በበለጠ ይጨምረዋል ተብሏል።

ታዋቂዎቹ የሆሊውድ ተዋናዮች በማደጎ ከኢትዮጵያ የወሰዷትን የ17 አመቷን ዘሃራን ጨምሮ፣ ፓክስ፣ ሺሎህና ቪቪየንና ኖክስ የተባሉ መንትዮች ወላጆች ናቸው።

የ19 አመቱ ማዶክስ እድሜው 19 በመሆኑ ከዚህ የፍርድ ቤቱ ውሳኔ አልተካተተም።

የፍርድ ቤቱን ውሳኔ በመቃወም አንጀሊና ጆሊ ህጋዊ ትግሏን እንደምትቀጥል ፔጅ ሲክስ የተባለ ድረ-ገፅ አንድ ምንጭ ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።

Leave a Comment

Related Posts

en_USEnglish