Home Entertainment News ናኦሚ ኦሳካ ለመገናኛ ብዙሃን አልናገረም በማለቷ ከውድድሮች ልትታገድ ትችላለች ተባለ

ናኦሚ ኦሳካ ለመገናኛ ብዙሃን አልናገረም በማለቷ ከውድድሮች ልትታገድ ትችላለች ተባለ

by sam

የዓለም ቁጥር ሁለቷ የሜዳ ቴኒስ ተጫዋች ናኦሚ ኦሳካ ለመገናኛ ብዙሃን ለመናገር ፈቃደኛ አለመሆኗን ከቀጠለች የፈረንሣይ ኦፕንን ጨምሮ ወደፊቱ ከሚደረጉ የግራንድ ስላም ውድድሮች እንደምትባረር አዘጋጆቹ ተናግሩ።

ጃፓናዊቷ ኦሳካ ባለፈው ሳምንት የአዕምሮ ጤንነቷን ለመጠበቅ ስትል በሮላንድ ጋሮስ (የፈፈረንሳይ ኦፕን ሌላኛው ስም) ውድድር ወቅት ምንም ዓይነት መግለጫ እንደማትሰጥ ገልጻለች።

እሑድ ሮማኒያዊቷን ፓትሪሺያ ማሪያ ቲግን በውድድሩ የመጀመሪያ ዙር አሸንፋ መግለጫ ባለመስጠቷ 15,000 ዶላር ተቀጥታለች፡፡

የዓለም ቁጥር ሁለቷ ውድድሩን 6-4 7-6 (7-4) አሸንፋለች፡፡

የአራቱ ግራንድ ስላም አዘጋጆች በጋራ በሰጡት መግለጫ ኦሳካ፤ “ተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት እና ወደፊቱ ከግራንድ ስላም ውድድሮች ልትታገድ ትችላለች” ብለዋል፡፡

ኦሳካ እሁድ ዕለት “ለውጥ ሰዎችን ምቾት እንዳይኖራቸው ያደርጋል” ስል በትዊተር ገጿ አስፍራለች።

Leave a Comment

Related Posts

en_USEnglish