Home Entertainment News ናሳ ምርምር ለማድረግ ሁለት ልዑኮችን ወደ ቬኑስ እንደሚልክ ገለጸ

ናሳ ምርምር ለማድረግ ሁለት ልዑኮችን ወደ ቬኑስ እንደሚልክ ገለጸ

by sam

ናሳ የስነ ምድርና የከባቢ አየር ምርምር ለማድረግ ሁልት ልዑኮችን ወደ ቬኑስ እንደሚልክ አስታወቀ

እንደ አውሮፓውያኑ የዘመን ቀመር በ2028 ና 2030 ወደ ቬኑስ ለሚደረጉት ተልዕኮዎች እያንዳንዳቸው 500 ሚሊዮን ዶላር እንደሚወጣባቸውም ተገልጿል።

የናሳ አስተዳዳሪ ቢል ኔልሰን ተልዕኮዎቹ “ከ 30 ዓመታት በላይ ያልደረስንበትን ፕላኔት ለመመርመር እድል ይሰጡናል” ብለዋል፡፡

በፕላኔቷ ላይ ለመጨረሻ ጊዜ ምርምር የተደረገው እንደ አውሮፓውያኑ 1990 ነበር።

ናሳ ተልዕኮዎቹን ለመፈጸም ከውሳኔ ላይ የደረሰው የተለያዩ ግምገማዎችን ካከናወነ፣ ያላቸውን ሳይንሳዊ አስፈላጊነትና አዋጭነት ካረጋገጠ በኋላ ነው ተብሏል፡፡

ታዲያ “እነዚህ ሁለት ጥምር ተልእኮዎች ቬኑስ እንዴት እርሳስ [lead] ማቅለጥ የሚችል የእሳትን ገጽታ የተላበሰ ዓለም ሊሆን እንደቻለ ለመረዳት ዓላማ ያደረጉ ናቸው ሲሉ አስተዳዳሪው ኔልሰን አስረድተዋል፡፡

ቬኑስ ከጸሀይ በመቀጠል ሁለተኛዋ ሞቃታማ ፕላኔት ስትሆን እስከ 500 ሴልሺየስ የምትሞቅና እራሳስን ማቅለጥ የሚችል የአየር ሁኔታ ላይ ያላት የምትገኝ ናት።

Leave a Comment

Related Posts

en_USEnglish