Home Entertainment News አፕል የተጠቃሚዋን ስልክ ለመሥራት ወስዶ ፎቶዋን በማጋራቱ ሚሊዮን ዶላሮች ተቀጣ

አፕል የተጠቃሚዋን ስልክ ለመሥራት ወስዶ ፎቶዋን በማጋራቱ ሚሊዮን ዶላሮች ተቀጣ

by sam

ግዙፉ አሜሪካዊ የቴክኖሎጂ ኩባንያ አፕል ሠራተኛው ስልኳን ለማሠራት ያመጣች አንዲት ተጠቃሚ ፎቶን በማጋራቱ ድርጅቱ በርካታ ሚሊዮን ዶላር ከፍሏል።

አይፎን ስልክ ያላት ግለሰብ ስልኳን ለማሠራት ነበር ወደ አንድ የአፕል ሱቅ የመጣችው።

ነገር ግን የተጠቃሚዋ ግላዊ ፎቶዎች በፌስቡክና ሌሎች ማሕበራዊ ድር አምባዎች ላይ ልክ እሷ እንደለጠፈችው ተደርገው ተቀምጠዋል።

ይህ ጉዳይ ወደ መገናኛ ብዙሃን ሲመጣ መጀመሪያ የአፕል ስም አልተጠቀሰም ነበር።

አሁን አፕል ጉዳዩን አምኖ በይፋ ይቅርታ ጠይቋል።

መግለጫ የለቀቀው አፕል “የተጠቃሚዎቻችንን ግላዊ መረጃ መጠበቅን በጣም እናከብራለን። ሰዎች ስልኮቻቸውን ሲያሠሩ መረጃዎቻቸው እንዴት ሊጠበቁ ይችላሉ የሚለውን በተለመከተ ያወጣነው መመሪያ አለ” ብሏል።

ሁኔታው የተከሰተው በፈረንጆቹ 2016 ሲሆን አፕል ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ሁኔታውን በቅርበት እየተከታተለ እንደነበር አስታውቋል።

ጉዳዩን ለመጀመሪያ ጊዜ የዘገበው ዘ ቴሌግራፍ የተሰኘው ጋዜጣ ነበር።

በኦሬጎን ዩኒቨርሲቲ ተማሪ የሆነችው ግለሰብ ስልኳ እንዲሠራላት የአፕል ስልኮች ሠሪ ወደ ሆነው ፔጋትሮን ቴክኖሎጂ ሰርቪስ የተሰኘ ሱቅ ስልኳን ልካ ነበር።

አፕል በጉዳዩ እጃቸው አለበት ያላቸውን ሁለት የስልክ ጥገና ሠራተኞች እንዳባረረ ተዘግቧል።

በተጨማሪም በዚህ ጉዳይ ስሙ እንዳይነሳ ጠይቆ የነበረ ቢሆንም ፔጋትሮን የተሰኘው ኩባንያ ለአፕል የካሳ ክፍያ በከፈለበት ወቅት ነው የግዙፉ ድርጅት ስም ይፋ የወጣው።

ከሁለት ዓመታት በፊትም በተመሳሳይ አንድ የአፕል ስልኮች ጠጋኝ ስልኳ እንዲሠራላት ካመጣች ሴት የፎቶ ማህደር ውስጥ ገብቶ ግላዊ ፎቶዎችን ወደ ራሱ መላኩ ተዘግቦ ነበር።

በወቅቱ አፕል ወዲያውኑ ጉዳዩን እየመረመረ እንዳለና እጁ አለበት የተባለው ግለሰብ ሥራውን እንዳጣ አሳውቆ ነበር።

ሁኔታው አሜሪካ ውስጥ ስልክ ለጥገና ወደ ሱቅ መወሰድ የለበትም ብለው ለሚከራከሩ ሰዎች ጥሩ አጋጣሚ ሆኖላቸዋል።

ከአሜሪካ ግዛቶች 20ዎቹ ‘ራይት ቱ ሪፔይር’ የተሰኘው ረቂቅ ለውሳኔ አቅርበዋል። ረቂቁ አፕልን የመሳሰሉ ግዙፍ ድርጅቶች ስልክ ሲያመርቱ ለጥገና የሚሆኑ ቁሳቁሶችን ለሦስተኛ ወገን ጠጋኞች እንዲሰጡ ያስገድዳል።

Leave a Comment

Related Posts

en_USEnglish