Home Entertainment News የጀምስ ቦንድ አዲሱ ፊልም በመጀመሪያው ቀን 5 ሚሊዮን ፓውንድ ማስገባቱ ተሰማ

የጀምስ ቦንድ አዲሱ ፊልም በመጀመሪያው ቀን 5 ሚሊዮን ፓውንድ ማስገባቱ ተሰማ

by sam

‘ኖ ታይም ቱ ዳይ’ (No time to die) የተሰኘው የጀምስ ቦንድ አዲሱ ፊልም በዩኬ ቦክስ ኦፊስ የመጀመሪያ ቀን እይታ 5 ሚሊዮን የእንግሊዝ ፓውንድ ገቢ አግኝቷል።

የዳንኤል ክሬግ ወይም የጄምስ ቦንድ የመጨረሻው ፊልም እንደሆነ የተነገረለት ”ኖ ታይም ቱ ዳይ’ በእንግሊዝ እና በአይሪሽ ሲኒማ ቤቶች በመጀመሪያው ቀን ከ 4.5 እስከ 5 ሚሊዮን ፓውንድ ሳያስገባ እንዳልቀረ የፊልሙ ፕሮዲውሰሮች ገምተዋል።

ፊልሙ ለእይታ የሚበቃበት ቀን በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት በተደጋጋሚ የተቀየረ ሲሆን የፊልሙ መውጣት የቦክስ ኦፊስ እይታን በመጨመር ተቀዛቅዞ የቆየውን የፊልም ኢንደስትሪ ወደ ነበረበት እንደ ሚመልሰው እየተጤነ ይገኛል።

ባለፈው ሐሙስ አዲሱን ፊልም የተመለከቱት ሰዎች ቁጥር ከ2015 ተመልካች በ13 በመቶ የበለጡት ቢሆንም በ2012 ጀምስ ቦንድ ያወጣውን ‘ስካይፎል’ን ከተመለከቱት በ26 በመቶ ያነሰ እንደሆነ ዩኒቨርሳል ፒክቸርስ የተሰኘው የፊልም ተቋም አስታውቋል። በተጨማሪም አዲሱ ፊልም በዩኬ “ከማንኛውም ፊልም በላይ በስፋት የተለቀቀ” እንደሆነም ተነግሯል።

Leave a Comment

Related Posts

en_USEnglish