Home Entertainment News የላይቤሪያው ፕሬዝዳንት ጆርጅ ዊሃ የኮሮና ቫይረስን በተመለከተ ግንዛቤ ለመፍጠር ሙዚቃ አቀነቀኑ።

የላይቤሪያው ፕሬዝዳንት ጆርጅ ዊሃ የኮሮና ቫይረስን በተመለከተ ግንዛቤ ለመፍጠር ሙዚቃ አቀነቀኑ።

by sam

የላይቤሪያው ፕሬዝዳንት ጆርጅ ዊሃ፣ በሙዚቃ በመሣሪያነት በመጠቀም፣ በድህነት እጅጉን በተጠቃችው የምዕራብ አፍሪካዋ ሃገር ውስጥ በሽታን የመከላከል እርምጃዎችን አስመልክቶ ግንዛቤን ለማሳደግ በኮሮና ቫይረስ ላይ የሚያውጠነጥን ነጠላ ዜማ ለቀዋል።

ላይቤሪያው ፕሬዝዳንት ጆርጅ ዊሃ የኮሮና ቫይረስን በተመለከተ ግንዛቤ ለመፍጠር ሙዚቃ አቀነቀኑ።

የላይቤሪያው ፕሬዝዳንት ጆርጅ ዊሃ፣ በሙዚቃ በመሣሪያነት በመጠቀም፣ በድህነት እጅጉን በተጠቃችው የምዕራብ አፍሪካዋ ሃገር ውስጥ በሽታን የመከላከል እርምጃዎችን አስመልክቶ ግንዛቤን ለማሳደግ በኮሮና ቫይረስ ላይ የሚያውጠነጥን ነጠላ ዜማ ለቀዋል።

“ሌትስ ስታንድ ቱጌዘር ኤንድ ፋይት ኮሮና ቫይረስ” ወይም “በአንድነት ቆመን ኮሮና ቫይረስን እንታገል” በሚለው ሙዚቃቸው፣ ዊሃ እንስት ድምፃዊያን በህብር እየተቀበሏቸውና ዘ ራባይስ በሚባለው የሙዚቃ ቡድን የጊታር ዜማ እየታጀቡ፣ ስለኮሮና ቫይረስ ስርጭት ያብራራሉ እንዲሁም እጅ መታጠብን በአዕንዖት ያበረታታሉ። 

ስድስት ደቂቃ ያህል የሚፈጀው ይህ ሙዚቃ ከዚህ ሌላ የበሽታውን ምልክቶች ይገልጽና ኮቪድ19 በአብዛኛው የሚተላለፈው ሰዎች “በተበከሉ እጆቻቸው ሌሎች እጆችን፣ አፍንጫቸውን እና ዓይኖቻቸውን በሚነኩበት ጊዜ” መሆኑን ጨምሮ ያብራራል። 

Leave a Comment

Related Posts

en_USEnglish