Home Entertainment News ለ50 ዓመታት ሳይፈታ የቆየውን የሒሳብ እንቆቅልሽ በቀናት ውስጥ የፈታችው ተማሪ

ለ50 ዓመታት ሳይፈታ የቆየውን የሒሳብ እንቆቅልሽ በቀናት ውስጥ የፈታችው ተማሪ

by sam

አሜሪካዊቷ የዩኒቨርስቲ ተማሪ ለ50 ዓመት የበርካቶችን አእምሮ የፈተነውንና ሳይፈታ የቆየውን የሒሳብ ቀመር በቀላሉ፣ በጥቂት ቀናት ውስጥ፣በትርፍ ሰዓቷ ፈትታዋለች። ሊሳ ፒኪሪሎ ሦስተኛ ዲግሪዋን በዩኒቨርስቲ ኦፍ ቴክሳስ እየሰራችነው። ከዩኒቨርስቲ ፕሮፌሰሯ ካሜሮን ጎርደን ጋር እያወራች በነበረበት ወቅት እግረመንገዷን ለወሬያቸው ማጣፈጫ በሚል የሰራችውን የሒሳብ ስሌት፣ያቃለለችውን የሒሳብ ቀመር አነሳች። “መጮህ ጀመረ ‘እንዴት በጣም ደስተኛ አልሆንሽም?'” እንዳላት ፒኪሪ ሎበኳንታ ለሚታተመው የሳይንስ ዜናን የሚሰራጨው ድረገጽ ተናግራለች። “እብድነው የሆነው” በማለትም የነበረውን ሁኔታ ያስታወሰችው። ወይዘሪት ፒኪሪሎ ሦስተኛ ዲግሪዋን ሳትይዝ የረዳት ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ያሰጣት የሒሳብ ቀመር ‘ኮንዌይኖት ፕሮብሌም’ ይሰኛል። ኮንዌይኖት ፕሮፕሌም(Conway knot problem) በብሪታንያዊው ሒሳብ ሊቅ ጆንሆርቶን ኮንዌይ በ1970 የተቀመረነው። ፒካሪሎ ግን ስለዚህ መልመጃ የሰማችው ለመጀመሪያ ጊዜ እአአ በ2018 በአንድ ሴሚናር ላይ መሆኑን ታስታውሳለች። ፕሮፌሰር ጎርደን “ምንያህል እድሜ ጠገብ ዝነኛ የሒሳብ መልመጃ መሆኑን ያወቀች አይመስለኝም” ብለዋል የወይዘሪት ፒኪሪሎ ሥራ በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ የታተመ ሲሆን እርሷም ይህንን የጥያቄ ጎምቱ፣የመልመጃዎች አውራ በመፍታቷ በማሳቹሴት ኢንስቲትዩት ኦፍ ቴክኖሎጂ የረዳት ፕሮፌሰርነት ማዕረግ አግኝታለች።

Leave a Comment

Related Posts

en_USEnglish