Home Entertainment News የሲንጋፖር አየር መንገድ የቆሙ አውሮፕላኖቹን ምግብ ቤት አደረገ

የሲንጋፖር አየር መንገድ የቆሙ አውሮፕላኖቹን ምግብ ቤት አደረገ

by sam

ሲንጋፖራውያን ምሳቸውን ለመመገብ ወደ አየር መንገድ ጎራ ብለው አንድ ጥግ የቆመ A380 ኤርባስ አውሮፕላን ውስጥ መሰየም ብቻ ይጠበቅባቸዋል። በአውሮፕላኑ ውስጥ ምሳቸውን ለመመገብ የቋመጡ ሰዎች ለሁለት ቀን የተዘጋጀውን ወንበር ሙሉ በሙሉ ይዘውታል። በዚህ አውሮፕላን ውስጥ ገብቶ ለመመገብ 496 የአሜሪካ ዶላር መክፈል ይጠበቃል።

አየር መንገዱ አገልግሎቱን ፈላጊዎች ስለበዙበት ሁለት ተጨማሪ ቀናትን ምሳና እናት ለማስተናገድ በማሰብ መጨመሩን አስታውቋል። የሲንጋፖር አየር መንገድ በኮሮናቫይረስ ምክንያት ገበያ አጥተው ፈተና ውስጥ ከወደቁ እና ሌሎች አማራጭ ከሚፈልጉ አየር መንገዶች መካከል አንዱ ነው።

አየር መንገዱ በአሁን ሰዓት ሁለት A380 ኤር ባስ አውሮፕላኖችን ለሶስት ሰዓት የምግብ መስተንግዶ እንዲሰጡ ለመጠቀም አቅዷል።ሁለቱም አውሮፕላኖች አካላዊ ርቀትን ለመጠበቅ በሚያስችል መልኩ ተደራጅተው በግማሽ አቅማቸው ብቻ ደንበኞችን ያስተናግዳሉ።

Leave a Comment

Related Posts

en_USEnglish