Home Entertainment News 2ሺህ ዓመታትን ያስቆጠረ የድመት ቅርጽ በፔሩ ተራራማ ስፍራ ላይ ተገኘ።

2ሺህ ዓመታትን ያስቆጠረ የድመት ቅርጽ በፔሩ ተራራማ ስፍራ ላይ ተገኘ።

by sam

የድመቱ ቅርጽ ይተገኘበት ስፍራ በዩኔስኮ የዓለም ቅርስ ተብሎ የተመዘገበ ቦታ ሲሆን በርካታ የመሬት ላይ ቅርሶችን የያዘ ቦታ ነው። ቅርሶቹም እስከ 2000 ዓመታት ድረስ ያስቆጠሩ ናቸው።

ተመራማሪዎች እንደገለጹት ይህ ትልቅ የድመት ቅርስ በከፍታ ቦታው ላይ የተሰራው ደማቅ ቀለም ያለውን የበረሃ አፈር በመጠቀም ነው።የድመቱ ቅርጽም እስከዛሬ ድረስ ሳይታወቅ ቆይቷል። በቅርቡ ግን በከፍታ ቦታው ላይ የምርምር ቦታ ለማቋቋም በማሰብ መንገድ ለመስራት ሲሞከር ነው ግዙፉ የድመት ቅርጽ የተገኘው።

በከፍታ ቦታው ላይ ጋደም ያለው ድመት ቅርጽ አካባቢው ለመጎብኘት ለሚመጡ ሰዎች ምቹ ቦታ ሊሆን እንደሚችል ተገምቷል።

Leave a Comment

Related Posts

en_USEnglish