Home Entertainment News የሞሮኮው ንጉሥ በፓሪስ የ3.5 ቢሊዮን ብር ቤት ገዙ

የሞሮኮው ንጉሥ በፓሪስ የ3.5 ቢሊዮን ብር ቤት ገዙ

by sam

በፈረንሳይ ዋና ከተማ ፓሪስ ከዝነኛው ኤፈል ታወር በቅርብ ርቀት የሚገኝ እጅግ የተቀናጣ ቤት ነው ንጉሡ የገዙት፡፡ ቤቱ 12 ‹ፈረስ ያስጋልባሉ› የተባለላቸው መኝታ ክፍሎች አሉት፡፡ የጌም መጫወቻ፣ ሰፊ መዋኛ፣ የግል አረንጓዴ ስፍራ እና በርካታ መኪናዎችን የሚይዙ መካነ ተሸከርካሪ (ፓርኪንግ) አሉት፡፡

ንጉሥ  መሐመድ 6ኛ በዓለም ላይ ካሉ ንጉሣዊ ቤተሰቦች ከብልጹጎቹ ተርታ እንደሆኑ ይነገራል፡፡ የግል ሀብታቸው ከታላቋ ብሪታኒያ ንግሥት ዳግማዊት ንግሥት ኤልዛቤጥ ጋር ብናወዳድረው በ10 እጥፍ ይበልጣል፡፡ ንጉሥ መሐመድ ይህንን ውድና ቅንጡ ቤት የገዙት የሞሮኮ ኢኮኖሚ በ6 በመቶ በወረደበት አስቸጋሪ ወቅት ነው። ንጉሥ መሐመድ ለፓሪሱ ቤታቸው 94 ሚሊዮን ዶላር ወይም ወደ 3.5 ቢሊዮን የኢትዮጵያ ብር ፈሰስ አድርገዋል ማለት ነው፡፡

Leave a Comment

Related Posts

en_USEnglish