Home Entertainment News የኢትዮጵያ አየር መንገድ ”የአፍሪካ ምርጥ የጭነት አየር መንገድ” ተብሎ ተመረጠ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ”የአፍሪካ ምርጥ የጭነት አየር መንገድ” ተብሎ ተመረጠ

by sam

 የኢትዮጵያ አየር መንገድ የ2020 ”የአፍሪካ ምርጥ የጭነት አየር መንገድ” ተብሎ መመረጡን አስታወቀ፡፡

የአየር መንገዱ የጭነትና የሎጂስቲክ አገልግሎት በአፍሪካ ያለው መዳረሻ ከፍተኛ ሲሆን፤ በተደጋጋሚ ”ምርጥ የጭነት አየር መንገድ” በመባል አሸንፏል፡፡

አየር መንገዱ በጭነት አገልግሎቱ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር የ2020 ”የአፍሪካ ምርጥ የጭነት አየር መንገድ” ተብሎ በመመረጥ ተሸላሚ ሆኗል፡፡

አየር መንገዱ በዘርፉ በአህጉሪቱ የሚሰጠው አገልግሎት የላቀ መሆኑም ተገልጿል፡፡

ሽልማቱን የተቀበሉት የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጭነትና የሎጂስቲክ አገልግሎት ኃላፊ አቶ ፍፁም አባዲ ባስተላለፉት መልዕክት አየር መንገዱ የአቪዬሽን ኢንዱስትሪው ፈተና ላይ በሆነበት በዚህ ወቅት ለሽልማቱ መመረጡ ጥንካሬውን እንደሚያሳይ ገልጸዋል።

”የሰራተኞቻችን ጥንካሬ፣ ዘመናዊ አውሮፕላኖቻችንና ደረጃውን የጠበቀው መሰረተ ልማታችን በብቃት እንድንቀሳቀስ አስችሎናል’’ ብለዋል።

የተቋሙ ኃላፊዎችም ከወቅቱ ጋር በመራመድ የሚሰጡት አመራር የኮቪድ-19 ወረርሽኝን በመቋቋም ለስኬት እንዳበቃው ተናግረዋል።

ሽልማቱ አየር መንገዱ ሥራውን በብቃት ለማከናወን እንደሚያስችለው ጠቁመዋል።

”የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጭነትና የሎጀስቲክ አገልግሎት ኮቪድ-19 ከተከሰተ ጀምሮ እጅግ አስፈላጊ የሆኑ የሕክምና ቁሳቁስን በመላው አፍሪካና ወደ ተቀረው ዓለም በማጓጓዝ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ አጋርነቱን በሚገባ አሳይቷል” ሲሉ አቶ ፍጹም ተናግረዋል፡፡

Leave a Comment

Related Posts

en_USEnglish