Home Entertainment News ህንዳዊው ዶክተር ‘የአላዲን ኩራዝ’ በሚል 41 ሺህ 500 ዶላር ተጭበረበረ

ህንዳዊው ዶክተር ‘የአላዲን ኩራዝ’ በሚል 41 ሺህ 500 ዶላር ተጭበረበረ

by sam

በህንዷ ኡታር ፕራዴሽ ግዛት ሁለት ግለሰቦች ጤናና ሃብት ያመጣል ያሉትን የአላዲንን ኩራዝ በ41 ሺህ 500 ዶላር ለአንድ ዶክተር መሸጣቸውን ተከትሎ ከስ ተመስርቶባቸዋል።

ግለሰቦቹ ኩራዙን ከገዛህ “ሃብት ያትረፈፍርልሃል ጤናንም ይሰጥሃል” ብለው አጭበርብረዋል በሚልም ነው የተከሰሱት።

በተረቶች ላይ የሚታወቀውን የአላዲንን ኩራዝ እውነተኛ በማስመሰል ‘ጂኒ ለማስወጣትም መሞከራቸውንም የህንድ ሚዲያዎች ዘግበዋል።

በመጀመሪያ ግለሰቦቹ ጠይቀውት የነበረው ብር 200 ሺህ ዶላር ሲሆን ዶክተሩ 41 ሺህ 500 ዶላር የመጀመሪያ ክፍያ በመስጠት ቀሪውን ሌላ ጊዜ እንደሚከፍልም ነግሯቸዋል።

ከዚህም ጋር በተያያዘ አንዲት ሴት ተሳትፋለች የተባለች ሲሆን ተጠርጣሪዋንም ፖሊስ በመፈለግ ላይ ነው።

ዶክተሩ በዚህ ሳምንት ለፖሊስ ሪፖርት ባደረገው መሰረት ሁለቱን ግለሰቦች ያገኛቸው እናታቸውን ሲያክም መሆኑንም የህንዱ ኤንዲቲቪ ሚዲያ ዘግቧል።

የግለሰቦቹን እናት ለአንድ ወር ያህልም በሚያክምበት ወቅት አንድ አዋቂ ግለሰብ ቤታቸው እየመጣ እንደሚጠይቃቸውና የተለያዩ ተአምራቶችንና ፈውሶችን እንደሚያከናውን በመንገርም ቀስ በቀስ እንዳሳመኑት ተገልጿል።

ከዚያም በኋላ ይህንን አዋቂ የተባለውን ግለሰብም ጋር መገናኘቱን ተናግሯል።

በአንድ ወቅትም “አላዲንን በአካል እንዳየውና ፊት ለፊቱም መቆሙን የሚናገረው ዶክተር በኋላ ግን አንደኛው ተጠርጣሪ ግለሰብ እንደ አላዲን ለብሶ መምጣቱን መረዳት ችሏል።

ሌሎች የህንድ ሚዲያዎችም እንዲሁ ተጠርጣሪዎቹ ጅኒ ለማውጣት መሞከራቸውን ዘግበዋል።

ሃብትና ንብረት ያመጣልሃል እንዲሁም ጤንነትህ የተሟላ ይሆናልም ብለው ቃል በመግባት 15 ሚሊዮን የህንድ ሩፒ (200 ሺህ የአሜሪካን ዶላር) ከጠየቁት በኋላ 41 ሺህ 500 ዶላር ክፍያ መስማማታቸውም ተገልጿል።

በሜሩት የሚገኙ የፖሊስ ኃላፊ አሚት ራይ ሌሎች ግለሰቦችም እንዲሁ ሌሎች ቤተሰቦችን እያጭበረበሩ መሆናቸውንም ኤንዲ

Leave a Comment

Related Posts

en_USEnglish