Home Entertainment News ዶ/ር ቴድሮስ አድሐኖም በኮቪድ-19 ጥርጣሬ ራሳቸውን እንዳገለሉ አስታወቁ

ዶ/ር ቴድሮስ አድሐኖም በኮቪድ-19 ጥርጣሬ ራሳቸውን እንዳገለሉ አስታወቁ

by sam

የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተሩ ዶ/ር ቴድሮስ አድሐኖም ኮቪድ-19 ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ ስለነበራቸው እራሳቸውን አግልለው ለመቆየት መወሰናቸውን አስታወቁ። 

ዶ/ር ቴድሮስ በአሁኑ ሰዓት በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኙ እና ምንም አይነት የበሽታው ምልክት እንዳልታየባቸው በትዊተር ገፃቸው ላይ ይፋ አድርገዋል።

የ55 ዓመቱ ዶ/ር ቴድሮስ አድሐኖም እ.ኤ.አ 2017 ጀምሮ ላለፉት ሦስት ዓመታት የዓለም ጤና ድርጅትን በዋና ዳይሬክተርነት እየመሩ ይገኛሉ።

ዶ/ር ቴድሮስ ኮቪድ-19 ወረርሽኝ ከተከሰተ ጀምሮ ወረርሽኙን ለመቆጣጠር ኃላፊነታቸውን ሲወጡ መቆየታቸው ይታወቃል።

Leave a Comment

Related Posts

en_USEnglish