Home Entertainment News ”የሩጫ -ብስክሌት -የዱላ ቅብብል” ውድድር በእንጦጦ ፓርክ ሊካሄድ ነው

”የሩጫ -ብስክሌት -የዱላ ቅብብል” ውድድር በእንጦጦ ፓርክ ሊካሄድ ነው

by sam

“የሩጫ -ብስክሌት- የዱላ ቅብብል’’ ውድድር በእንጦጦ ፓርክ እንደሚያካሂድ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አስታወቀ። 

በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በሚካሄደው ውድድር በአንድ ቡድን አራት ሰዎች ይካፈሉበታል።

ከአራቱ ሰዎች ሁለቱ ብስክሌተኞች ፣ቀሪዎቹ ሁለቱ ደግሞ ሯጮች እንደሚሆኑ ተገልጿል።

ብስክሌተኞቹ 8 ኪሎ ሜትር፣ ሯጮች ደግሞ ሁለት ኪሎ ሜትር ርቀት የሚሸፍኑበትን ውድድር ያደርጋሉ።

በውድድሩ ለመሳተፍ 30 ቡድኖች የተመዘገቡ ሲሆን፣ በዚህም 120 ሰዎች እንደሚካፈሉ እና ህዳር 6 ቀን 2013 ውድድሩ እንደሚካሄድ  ኢዜአ ዘግቧል።

Leave a Comment

Related Posts

en_USEnglish