Home Entertainment News በኒው ዮርክ ግዛት ሳምራ ብሩክ ለሴኔት መቀመጫ ማሸነፏ ተሰማ፡፡

በኒው ዮርክ ግዛት ሳምራ ብሩክ ለሴኔት መቀመጫ ማሸነፏ ተሰማ፡፡

by sam

ኖቬምበር 3 በተካሄደው የአሜሪካ ምርጫ ከትውልደ ኢትዮጵያዊ ወላጆቿ በኒው ዮርክ ግዛት ሮችስተር የተወለደችው ሳምራ ብሩክ በግዛቲቱ ሴኔት ለትውልድ ከተማዋ 55ኛ ዲስትሪክት የተመደበውን መቀመጫ ማሸነፏ ተሰማ፡፡

የዴሞክራቲክ ፓርቲ አባል የሆነችው ሳምራ ብሩክ በግዛቲቱ የሴኔት መቀመጫ ማሸነፏን ያወጀችው የሪፐብሊካን ፓርቲው ተቀናቃኟ የሆኑትን ክሪስቶፈር ሚሲክን 52.5 በመቶ ድምጽ በማግኘቷ ነው፡፡ 

ተቀናቃኟ ክሪስቶፈር ሚሲክ 47.8 በመቶ ድምጽ አግኝተዋል፡፡ 

ሳምራ ማሸነፏን እርግጠኛ ሆና በይፋ ያወጀችው የሞንሮ ወረዳ የዴሞክራቲክ ፓርቲው ደጋፊዎች የሰጧቸውን የቅድመ ምርጫ ቀን ድምፆች ታሳቢ በማድረግ መሆኑን ሮችስተርፈርስት የተሰኘው ድረ ገጽ ጽፏል፡፡ 

የሞንሮ ወረዳ የምርጫ ቦርድ ኃላፊዎች የወረዳው ነዋሪ የሆኑ 47,675 የተመዘገቡ ዴሞክራቶች ከምርጫው ቀን አስቀድመው ድምጽ መስጠታቸውን ተናግረዋል፡፡

ከሪፐብሊካኖቹ ወገን በተመሳሳይ መልኩ የተሰጡ ድምጾች 20,489 ብቻ ናቸው ተብሏል፡፡ 

የሳምራ ተቀናቃኝ የሆኑት ክሪስቶፈር ሚሲክ ሁሉም ድምጽ ተቆጥሮ እስከሚያልቅ ክትትል እንደሚያደርጉ ቢናገሩም የቆጠራው ውጤት የሳምራ ብሩክን አሸናፊነት ያስቀራል ብለው እንደማያምኑ አልሸሸጉም፡፡

Leave a Comment

Related Posts

en_USEnglish