Home Entertainment News ማይክሮሶፍት ለኦፊስ-2010 የደህንነት ዘመና ማቋረጡን ተከትሎ ተጠቃሚዎች ለሳይበር ጥቃት እየተጋለጡ እንደሆነ ተገለፀ

ማይክሮሶፍት ለኦፊስ-2010 የደህንነት ዘመና ማቋረጡን ተከትሎ ተጠቃሚዎች ለሳይበር ጥቃት እየተጋለጡ እንደሆነ ተገለፀ

by sam

ማይክሮሶፍት ኩባንያ ለኦፊስ (Office-2010) የደህንነት ማዘመኛ ማቅረብ ባለፈዉ ወር ማቋረጡን ተከትሎ ተጠቃሚዎች ለሳይበር ጥቃት እየተጋለጡ መሆኑን ቴክራዳር ድረ-ገጽ ዘግቧል፡፡

ለኦፊስ-2010 የሚቀርበዉ መደበኛ የደህንነት ክፍተት መጠገኛ መቋረጡ ኦፊስ-2010 የሚጠቀም ማንኛውም አካል በአዳዲስ አጥፊ ሶፍትዌር ጥቃቶች ተጋላጭ አድርጎታል፡፡ 

በመሆኑም የዊንዶዉስ ኦፊስ-2010 ተጠቃሚዎች ወደ ኦፊስ-2013 እና ከዛ በላይ ወደ ሆኑ የኦፊስ ምርቶች በማዘመን በራሳቸውና እና በተቋማቸው ላይ ሊደርስ የሚችልን የሳይበር ጥቃት ሊከላከሉ ይገባል ተብሏል፡፡ 

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲም ግለሰቦችም ይሁኑ ተቋማት ለሳይበር ጥቃት ተጋላጭ እንዳይሆኑ የሚጠቀሙባቸው ኮምፒውተሮችን ወደ ኦፊስ-2013 እና በላይ እንዲያዘምኑ መክሯል፡፡

Leave a Comment

Related Posts

en_USEnglish