Home Entertainment News ዘ ዊኬንድ ፣ አቤል ተስፋዬ የግራሚ ሽልማት “ሙሰኛ” ነው ሲል ተናገረ

ዘ ዊኬንድ ፣ አቤል ተስፋዬ የግራሚ ሽልማት “ሙሰኛ” ነው ሲል ተናገረ

by sam

ካናዳዊው ሙዚቀኛ ዘ ዊኬንድ፣ አቤል ተስፋዬ በሙዚቃው ኢንዱስትሪ ዘንድ ከፍተኛ ስፍራ የሚሰጠውን የግራሚ ሽልማት ሙሰኛ ነው አለ።ከዚህ ቀደም የግራሚ ሽልማቶችን ያሸነፈው ዘ ዊኬንድ ለዘንድሮው ዓመታዊ የግራሚ ሽልማትም አልታጨም።

ሙዚቀኛው ያወጣው አልበም ከፍተኛ ተቀባይነትን ማግኘቱን ተከትሎ እንዲሁም በተለይም በአልበሙ የተካተተው ‘ብላይንዲንግ ላይትስ’ የተሰኘው ዜማው ተወዳጅ የሙዚቃ ሰንጠረዦችን በአንደኛ ደረጃ መምራቱን ተከትሎ ለግራሚ ሽልማት መታጨት ብቻ ሳይሆን በርካታ ሽልማቶችን ያሸንፋልም ተብሎ ተጠብቆ ነበር።

“የግራሚ ሽልማት አሁንም ቢሆን ሙሰኛ ነው” በማለት በትዊተር ገፁ ላይ ያሰፈረው ሙዚቀኛው አክሎም “ለእኔም፣ ለአድናቂዎቼም ሆነ ለሙዚቃ ኢንዱስትሪው ሲባል ግልፅነትን እንጠብቃለን” ብሏል።

የግራሚ ሽልማት ኃላፊዎች በበኩላቸው የሙዚቀኛውን ቅር መሰኘት እንደተሰማቸው ገልፀው ነገር ግን በየዓመቱ ድንቅ ችሎታ ያላቸው ሙዚቀኞችም ሽልማት ላያገኙ ይችላል በማለት ምላሽ ሰጥተዋል። ‘አፍተር ሃወርስ’ የተሰኘው አልበሙ ከፍተኛ ሽያጭ በማስመዝገብ የዓመቱን ክብረ ወሰን የጨበጠ ሲሆን ‘ብላይንዲንግ ላይትስ’ የተሰኘውና በዚህ አልበም የተካተተው ሙዚቃው በአሜሪካ የሙዚቃ ሰንጠረዥን ለረዥም ጊዜ በመቆጣጠር ከአስሩ ምርጥ ተካቷል።

ከኢትዮጵያዊ ቤተሰቦች በካናዳ ተወልዶ ያደገው ዘ ዊኬንድ (አቤል ተስፋዬ) በቅርቡ በሙዚቃው ስፍራ ትልቅ ቦታ የሚሰጣቸውን ኤምቲቪ፣ ቪኤምኤና የአሜሪካ የሙዚቃ ሽልማቶችን አግኝቷል።

በየካቲት ወርም በአሜሪካውያን ዘንድ ከፍተኛ ስፍራ በሚሰጠው ሱፐር ቦውል የእግር ኳስ ጨዋታ በእረፍት ሰዓት ላይ ይዘፍናል ተብሎ ይጠበቃል።

Leave a Comment

Related Posts

en_USEnglish