Home Entertainment News ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ዶክተር ውለታ የ2020 የዌብ ሰሚት ዓለም አቀፍ ውድድር አሸነፉ

ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ዶክተር ውለታ የ2020 የዌብ ሰሚት ዓለም አቀፍ ውድድር አሸነፉ

by sam

 ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ የላሊበላ ኔትወርክ መስራች ዶክተር ውለታ ለማ ፖርቹጋል በተካሄደው የ2020 የዌብ ሰሚት ዓለም አቀፍ ውድድር ላይ አሸናፉ፡፡

በጤናው ዘርፍ ላይ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ28 ዓመታት ልምድ ያካበቱት ዶክተር ውለታ ከሽልማቱ በኋላ ይህ ድል የኔ ብቻ አይደለም በመላው አፍሪካ ለሚገኙ እናቶችና ህጻናት ጭምር ነው ብለዋል፡፡

እንዲሁም የኮሮና ቫይረስ በተከሰተበት ወቅት እንዲህ ያለ ሽልማት ማሸነፍ የተለየ ነው ብለዋል፡፡

ላሊበላ ግሎባል ኔትወርክ የጤና ዘርፉን ማዘመንና ዲጂታላይዝ የሚያደርግ ተቋም ሲሆን ለ20 ዓመታት ኢትዮጵያን ጨምሮ በሌሎች 

የአፍሪካ ሀገራት ላይ መስራቱ ነው የተነገረው፡፡

ተቋሙ በአፍሪካ ያለውን የጤና ስርዓት ከማዘመን በተጨማሪ ታካሚዎችን ማዕከል በማድረግ ይሰራል እንዲሁም የጤና ሁኔታን የሚያሳዩ መረጃዎችን ይመዘግባል፡፡

መስራቿ ይህንን ሽልማት የወሰዱት ከሌሎች 700 ስራ ፈጣሪዎች ጋር ተወዳድረው ነው ተብሏል፡፡

በፖርቹጋል የተዘጋጀውና ዶክተር ውለታ ያሸነፉበት ይህ የዌብ ኮንፍረንስ በዓለም ላይ ትልቁ መሆኑን መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

Leave a Comment

Related Posts

en_USEnglish