Home Entertainment News በቅርቡ ስልጣን የሚይዙት ፕሬዚዳንት ጆ ባይደንና ምክትላቸው ካሚላ ሃሪስ የታይም መጽሔት የዓመቱ ሰዎች በመባል ተመረጡ፡፡

በቅርቡ ስልጣን የሚይዙት ፕሬዚዳንት ጆ ባይደንና ምክትላቸው ካሚላ ሃሪስ የታይም መጽሔት የዓመቱ ሰዎች በመባል ተመረጡ፡፡

by sam

በቅርቡ ስልጣን የሚይዙት ፕሬዚዳንት ጆ ባይደንና ምክትላቸው ካሚላ ሃሪስ የታይም መጽሔት የዓመቱ ሰዎች በመባል ተመረጡ፡፡

ታይም በትዊተር መልዕክቱ የባይደንና ሃሪስ ጉዞ ታሪካዊ ነበር ሲል አስፍሯል፡፡

ባይደንና ሃሪስ ለዚህ የበቁት ኮቪድ በመከላከል ከፊት የቆሙ የጤና ባለሙያዎችንና የአሜሪካ የተላላፊ በሽታዎች ተቋም ኃላፊ አንቶኒዮ ፉቺ እና ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕን በመርታት ነው ተብሏል፡፡

የታይም መጽሔት ዋና አዘጋጅ ኤድዋርድ የአሜሪካንን ታሪክ በመቀየራቸው ከመከፋፈል ይልቅ የአብሮነት ኃይል እንደሚልቅ በማሳየታቸው ባይደንና ሃሪስ የ2020 የዓመቱ ሰው በመሆን መመረጣቸውን ነው በትዊተሩ ያሰፈረው፡፡

በ2016 ትራምፕ ወደ ስልጣን ሲመጡ በተመሳሳይ የዓመቱ ሰው መባላቸው ይታወቃል፡፡

ታይም በየዓመቱ በአሉታም ይሁን በአወንታ ተጽዕኖ ያሳረፉ ሰዎችን መምረጥ የጀመረው ከአውሮፓውያኑ 1927 ጀምሮ እንደነበር ይታወሳል፡፡

Leave a Comment

Related Posts

en_USEnglish