Home Entertainment News የአማዞኑ ጄፍ ቤዞስ የቀድሞ ባለቤት 4 ቢሊዮን ዶላር እርዳታ ሰጠች

የአማዞኑ ጄፍ ቤዞስ የቀድሞ ባለቤት 4 ቢሊዮን ዶላር እርዳታ ሰጠች

by sam

ማኬንዚ ስኮት ለምግብና አስቸኳይ ጊዜ የሚሆን 4 ቢሊዮን ዶላር እርዳታ ሰጠች። ገንዘቡ ከአንድ ግለሰብ በአራት ወራት ውስጥ ብቻ የተሰጠ ከፍተኛ እርዳታ ሆኖ ተመዝግቧል።

ማኬንዚ ስኮት በጦማሯ ላይ እንዳለችው ገንዘቡ በወረርሽኙ ምክንያት ኑሮ ዳገት የሆነባቸው አሜሪካዊያንን የሚያግዝ ነው።ማኬንዚ ስኮት በዓለም 18ኛዋ ሀብታም ናት።

በቅርቡም የሀብት መጠኗ በዚህ ዓመት ብቻ በ23 ቢሊዮን ዶላር ጨምሮ አሁን በድምሩ ወደ 60 ቢሊየን ዶላር ተመንድጎላታል።

አብዛኛው የሀብቷ ምንጭ ታዲያ ከቀድሞ ባለቤቷ ፍቺ በኋላ በፍርድ ቤት የተወሰነላት ገንዘብ ነው። ግለሰቧ የዓለም ቁጥር አንድ ሀብታም የአማዞኑ ጌታ ጄፍ ቤዞስ የቀድሞ ባለቤቱ መሆኗ ይታወቃል።

“ይህ ወረርሽኝ የብዙ አሜሪካዊያንን ሕይወት አመሳቅሏል” ያለለችው ስኮት ከ6500 የእርዳታ ድርጅቶች ውስጥ 380 የሚሆኑ የበጎ አድራጎት ድርጅቶችን ነቅሳ በማውጣት ገንዘቡን እንደሰጠች ገልጻለች።

Leave a Comment

Related Posts

en_USEnglish