Home Entertainment News የቺሊው ፕሬዚደንት የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ሳያደርጉ ‘ሰልፊ’ በመነሳታቸው ተቀጡ

የቺሊው ፕሬዚደንት የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ሳያደርጉ ‘ሰልፊ’ በመነሳታቸው ተቀጡ

by sam

ደቡብ አሜሪካዊቷ አገር ቺሊ ፕሬዚደንት ሴባስቲያን ፒኔራ የኮሮናቫይረስ ሕግን በመጣሳቸው 3 ሺህ 500 ዶላር ገንዘብ ተቀጡ።

ፕሬዚደንቱ ቅጣቱ የተጣለባቸው የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ሳያደርጉ ‘ሰልፊ’ በመነሳታቸው ነው።

ሰባስቲያን በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ ይኸው ከአንዲት የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ካላደረገች ሴት ጋር የተነሱት ፎቶ በስፋት ከተሰራጨ በኋላ ይቅርታ ጠይቀዋል።

ፕሬዚደንቱ በካቻጓ በሚገኘው ቤታቸው አቅራቢያ ባለ የባህር ዳርቻ ሴትዮዋ አብረዋት ፎቶ እንዲነሱ ስትጠይቃቸው “የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማድረግ ነበረብኝ” ብለዋል።

ቺሊ ሕዝብ በሚገለገልባቸው ቦታዎች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማድረግን የሚያዝ ጥብቅ ሕግ አላት።

ይህንን ሕግ መጣስም የገንዘብና የእስር ቅጣትን ጨምሮ ሌሎች ቅጣቶችን ያስከትላል።

Leave a Comment

Related Posts

en_USEnglish