Home Entertainment News 1ሺ ሄክታር የሚሰፋው የማይክል ጃክሰን የመኖርያ ግቢ በ22 ሚሊዮን ዶላር ተሸጠ

1ሺ ሄክታር የሚሰፋው የማይክል ጃክሰን የመኖርያ ግቢ በ22 ሚሊዮን ዶላር ተሸጠ

by sam

‘ዘ ኔቨርላንድ’ በሚል ስሙ የሚታወቀው የሟቹ ማይክል ጃክሰን መኖርያ ቤት መሸጡን ለጉዳዩ ቅርብ ነን የሚሉ ሰዎች ተናገሩ።

ይህ እጅግ ግዙፍ መኖርያ የሚገኘው ከሎስ ኦሊቮስ ከተማ ቀረብ ባለ ጫካ በካሊፎርኒያ ግዛት ውስጥ ነው።

ንብረቱን የገዙት ቢሊየነር ቤቱ ያወጣል ተብሎ ከተጠበቀው አንድ አራተኛውን ብቻ ከፍለው ነው የራሳቸው ያደረጉት።

ይህ የማይክል ጃክሰን የቀድሞ መኖርያ ግቢ እስከ 100 ሚሊዮን ዶላር ሊያወጣ ይችላል ተብሎ ተገምቶ ነበር።

ቤቱን የገዙት ቢሊየነር ሮን በርከል የሚባሉ ሰው ናቸው ተብሏል።

ዜናውን የዘገበው ዎል ስትሪት ጆርናል ሲሆን በዚህ ግዢኛ ሽያጭ በቀጥታ የተሳተፉ ሦስት ሰዎችን በምንጭነት ጠቅሷል።

ይህ የማይክል ጃክሰን ግቢ ስፋቱ 2ሺ 700 ኤከር ወይም 1ሺ 100 ሄክታር የሚሸፍን እጅግ ግዙፍ መኖርያ ግቢ ነው።

በካሊፎርኒያ ግዛት ከሳንታ ባራባራ ከተማ በስተ ሰሜን አቅጣጫ የሚገኘው ይህ እጅግ ግዙፍ መኖርያ ግቢ የማይክል ጃክሰንን ሞት ተከትሎ ሊሸጥ ዋጋ ሲወጣለት ለዓመታት ሲንከባለል ቆይቷል።

በ2015 የቤቱ ግምት 100 ሚሊዮን ዶላር የነበረ ሲሆን ባለፈው ዓመት ግን በ31 ሚሊዮን ዶላር ሊሸጥ ነው የሚሉ ዜናዎች መውጣት ጀምረው ነበር።

ማይክል ጃክሰን ቤቱን መጀመርያ ሲገዛው በ19 ሚሊዮን ዶላር ተኩል ነበር። የቤቱን ስምም በልጆች ዝነኛ የተረት ተረት ታሪክ ፒተር ፓን ውስጥ ባለው ደሴት ስም ሰይሞት ነበር።

Leave a Comment

Related Posts

en_USEnglish