Home Entertainment News በእንግሊዝ ከ200 ዓመት በፊት ተቆፍሮ ከወጣ ድንጋይ አዲስ ማዕድን ተገኘ

በእንግሊዝ ከ200 ዓመት በፊት ተቆፍሮ ከወጣ ድንጋይ አዲስ ማዕድን ተገኘ

by sam

ከ220 ዓመት በፊት ተቆፍሮ ከወጣ ድንጋይ “እጅግ አስደናቂ” በማለት ያወደሱትን አዲስ የማዕድን አይነት ማግኘታቸውን ተመራማሪዎች ገለፁ።

ጥቁር አረንጓዴ መልክ ያለው ማዕድን፣ ኬርኖዋይት የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል።

ማዕድኑ ስያሜውን ያገኘው ከኮርኒሽ ቋንቋ ኮርዎል ከሚለው ቃል ነው ተብሏል።

ከናቹራል ሂስትሪ ሙዚየም በተወጣጡ የማዕድን ባለሙያዎች ቡድን የተመራው ምርምር ከ200 ዓመት በፊት በእንግሊዝ ከሚገኘው ዊል ጎርላንድ የማዕድን ስፍራ ተቆፍሮ የወጣ ድንጋይ ላይ ጥናት ሲያደርጉ ማዕድኑን ማግኘታቸውን ማይክ ራምዚ ተናግረዋል።

ናቹራል ሂስትሪ ሙዚየም በእንግሊዝ አገር የሚገኝ ሲሆን በዓለም ላይ የተለያዩ ማዕድኖችን በሚገባ አከማችቶ የሚገኝ ነው። በአጠቃላይም 185 ሺህ የማዕድን ስብስቦችን ይዟል ተብሎ ተመዝግቧል።

ለዓመታት የማዕድን ባለሙያዎች አረንጓዴው ክሪስታል ሊሮሶናይት የተሰኘ ማዕድን ዓይነት መሆኑን ያምኑ የነበረ ቢሆንም ራምዚ እና ቡድናቸው ማዕድኑ የተለየ የኬሚካል ቅንብርና ውህደት እንዳለው መለየት ችለዋል።

ሰማያዊ ሊሮሶናይት በዓለም ላይ እጅግ ዋጋቸው ውድ ከሆኑ የማዕድን ዓይነቶች መካከል አንዱ ሲሆን አብዛኛው የሚመጣው ከዊል ጎርላንድ የማዕድን ስፍራ ነው።

ኮርንዎል በማዕድን ፍለጋ እና ቁፋሮ ታሪክ ውስጥ ቱባ ታሪክ ያለው እና በዩኔስኮ በዓለም ቅርስነት ደረጃ ስሙ ተመዝግቦ የሚገኝ ነው።

ራምዚ እንዳሉት “አብዛኞቹ እነዚህ ፍለጋዎች የተከናወኑት ከ100 ዓመት በፊት ነው፤ በተለይ ከአካባቢው ጋር ቁርኝት ያላቸውና በጣም ዝነኛ የሆኑት በጣም አስደናቂ ማዕድኖች ናቸው። በይበልጥ የማዕድን ፈላጊዎች፣ ሰብሳቢዎች ለዓመታት አገሪቱን የማዕድን ሀብት ለማግኘት ማሰሳቸውን ለተመለከተ በ2020 አዲስ ማዕድን መጨመራችን አስደናቂ ነው” ብለዋል።

Leave a Comment

Related Posts

en_USEnglish