Home Entertainment News ታዋቂው የቴሌቪዥን አቅራቢ ላሪ ኪንግ በኮቪድ-19 ተይዞ ሆስፒታል ገባ

ታዋቂው የቴሌቪዥን አቅራቢ ላሪ ኪንግ በኮቪድ-19 ተይዞ ሆስፒታል ገባ

by sam

ታዋቂው የቴሌቪዥን አቅራቢ ላሪ ኪንግ ኮሮናቫይረስ እንዳለበት በመረጋገጡ ሎስአንጀለስ ከተማ ውስጥ በሚገኝ ሆስፒታል ውስጥ ህክምና እየተደረገለት መሆኑን የአሜሪካ መገናኛ ብዙሃን ዘገቡ።

ለላሪ ኪንግ ቤተሰብ ቅርብ የሆኑ ምንጮች ለኤቢሲ ኒውስና ቀድሞ ይሰራበት ለነበረው ሲኤንኤን ቴሌቪዥን እንደተናገሩት ላሪ ሆስፒታል ከገባ ከሳምንት በላይ ሆኖታል።

ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የልብ ህመምን ጨምሮ በርካታ የጤና እክሎች ሲያጋጥሙት የነበረው ላሪ፤ ከ60 ዓመት በላይ በዘለቀው የቴሌቪዥን አቅራቢነት ሙያው በርካታ ሽልማቶችናና እውቅናዎችን አግኝቷል።

የ87 ዓመቱ ላሪ ተወካዮች እስካሁን በይፋ ወጥተው ሆስፒታል ስለመግባቱና አሁን ስላለበት ሁኔታ ምንም አይነት መግለጫ ስላልሰጡ ዝርዝር መረጃ የለም።

ላሪ ኪንግ መጀመሪያ ላይ እውቅናን ያገኘው በ1970ዎቹ በሬዲዮ ያቀርበው በነበረ ዝግጅቱ ነበር። ከዚያም ከ1985 እስከ 2010 (እአአ) በሲኤንኤን ቴሌቪዥን ላይ በተለያዩ መስኮች የዓለማችን ተጽእኖ ፈጣሪ ከሆኑ ታዋቂ ግለሰቦች ጋር በሚያደርገው ቃለ ምልልስ እውቅናን አትርፏል።

Leave a Comment

Related Posts

en_USEnglish