Home Entertainment News የጄምስ ቦንድ ፊልም ለዕይታ የሚበቃበት ቀን ለሶስተኛ ጊዜ ተራዘመ።

የጄምስ ቦንድ ፊልም ለዕይታ የሚበቃበት ቀን ለሶስተኛ ጊዜ ተራዘመ።

by sam

አዲሱ የጄምስ ቦንድ ፊልም ለዕይታ የሚበቃበት ቀን በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ለሶስተኛ ጊዜ ተራዘመ።

ኖ ታይም ቱ ዳይ (No Time To Die) የተሰኘው ይህ ፊልም ከዚህ ቀደም ሁለት ጊዜ የተገፋ ሲሆን አሁን በመጪው ዓመት ጥቅምት ወር ላይ ለዕይታ እንደሚበቃ ከፊልሙ ድረ ገጽ ማወቅ ተችሏል።

ከዚህ ቀደም ለዕይታ ይበቃል ተብሎ የነበረው ባለፈው ዓመት ሚያዚያ ወር ላይ ነበር።

ፊልሙ ጄምስ ቦንድን በዓብይ ገጸ ባህሪነት በመሳል ለዓለም ሕዝብ ሲያስኮመኩም 25ኛው ሲሆን እንግሊዛዊው እና የብሪቴይን 007 የደህንነት ባለሙያ ወይንም ሰላይ ሆኖ የሚሰራው ዳንዔል ክሬግ ደግሞ ለመጨረሻ ጊዜ በፊልሙ ላይ መተወኑ ነበር።

በፊልሙ ላይ ሊያ ሴይዱክስ እና ራሚ ማሌክ ተሳትፈውበታል።

Leave a Comment

Related Posts

en_USEnglish