Home Entertainment News የፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ ዘመን ቀዳማዊ ውሻ መሞቱን ተከትሎ ቤተሰቡ ሃዘን ላይ ነው

የፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ ዘመን ቀዳማዊ ውሻ መሞቱን ተከትሎ ቤተሰቡ ሃዘን ላይ ነው

by sam

የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ ውሻ መሞቱን ተከትሎ ኦባማ “ምርጥ ጓደኛችን” ሸኝተናል ብለዋል።

ውሻው ቦ ቅዳሜ ዕለት ነው ይህቺን ዓለም ለእነ ኦባማ ትቶ የተሰናበተው።

ሚሼል ኦባማ በማሕበራዊ ድር አምባቸው “ውሻችን ቦ ምርጥ የቤተሰባችን አባል ነበር” ብለዋል።

ቦ ወደ አሜሪካ መንግሥት መቀመጫ ዋይት ሃውስ የገባው በፈረንጆቹ 2009 ዓ.ም. ነበር።

ለኦባማና ሜሺል ሁለት ሴት ልጆች ይህ ጥቁርና ነጭ ቀለማት ያለው ይህ የፖርቹጋል ዘር የሆነ ውሻ በስጦታ የተሰጣቸው ለአዲስ ቤት መላመጃ ይሆናቸው ዘንድ ነው።

ባራክ ኦባማ በበኩላቸው “እጅጉን ያስፈልገን የነበረ ከሚጠበቅበት በላይ ያበረከተ ነበር” ሲሉ በማሕበራዊ ድር አምባቸው ስለውሻቸው መስከረዋል።

“በክፉ ቀናችን፣ በደስታችን እንዲሁም በተቀረው እኛን ሲያይ ደስ የሚለው ውሻችን ነበር” ብለዋል ኦባማ አክለው።

ከዶናልድ ትራምፕ በቀር ላለፉት 100 ዓመታት የአሜሪካ ፕሬዝደንቶች ወደ ዋይት ሃውስ ሲገቡ ኦፊሴላዊ ውሻ ነበራቸው።

የወቅቱ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ሁለት ውሻዎች አሏቸው። ምንም እንኳ ትንሹ ውሻ ሰው እየነከሰ ቢያስቸግርም።

የአሜሪካ ፕሬዝደንቶች ወደ ዋይት ሃውስ ይዘዋቸው የሚገቡ ውሻዎች ‘ቀዳማዊ ውሻ’ የሚል ስም ይሰጣቸዋል።

ሚሼል ኦባማ የቀድሞው ቀዳማዊው ውሻ ቦ ከዋይት ሃውስ ከወጡ በኋላም መልካም ጓደኛቸው እንደነበር ጠቅሰዋል።

“ቦ ከካንሰር ጋር ከታገለ በኋላ ነው ያረፈው” ብለዋል ሚሼል ፊርማቸው ባረፈበት የስንብት ድብዳቤያቸው።

Leave a Comment

Related Posts

en_USEnglish