Home Sport News ማንችስተር ሲቲዎች የፕሪሚየር ሊጉ ሻምፒዮን ሆኑ

ማንችስተር ሲቲዎች የፕሪሚየር ሊጉ ሻምፒዮን ሆኑ

by sam

ማንችስተር ሲቲ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ2020/21 የውድድር ዓመት ሻምፒዮን መሆናቸውን አረጋገጡ። 

ሲቲዎች ሻምፒዮን መሆናቸውን ያረጋገጡት ማንችስር ዩናይትድ በሜዳው በሌስተር ሲቲ 2 ለ 1 መሸነፉን ተከትሎ ነው። 

ሊጉ ሊጠናቀቅ ሦስት ጨዋታዎች ብቻ የቀሩት ሲሆን የደረጃ ሰንጠረዡን በሚመራው ማንችስተር ሲቲ እና ሁለተኛ ሆኖ በሚከተውለው ማንችስተር ዩናይትድ መካከል የ10 ነጥብ ልዩነት አለ።

ማንችስተር ዩናይትድ በቀሪ ጨዋታዎች ሲቲ ላይ እንደማይደርስ በመረጋገጡ ነው ሲቲዎች ሻምፒዮን መሆናቸውን ያረጋገጡት።

Leave a Comment

Related Posts

en_USEnglish