Home Sport News አጫጭር አለም አቀፍ ወቅታዊ መረጃዎች

አጫጭር አለም አቀፍ ወቅታዊ መረጃዎች

by sam

• የ መድፈኞቹ ግብ ጠባቂ አሮን ራምስዴል የ ክለቡ የወርሀ ጥቅምት ምርጥ ተጫዋች በመባል ተመርጧል ።

• ዳኒ ኤልቬስ ዳግም ለ ባርሴሎና ለመጫወት ከ ክለቡ ጋር በዚህ ሳምንት ድርድር እንደሚያደርግ ተገልጿል ።

• የ ፊፋ የ አመቱ ምርጥ ተጫዋቾች ሽልማት ጥር 9 በ ዙሪክ እንደሚካሄድ ይፋ ሆኗል ።

• ስፔናዊው የ መሐል ተከላካይ ሰርጅዮ ራሞስ ካጋጠመው የረጅም ጊዜ ጉዳት በኋላ ልምምድ መስራት ጀምሯል ።

• ፖል ፖግባ ከ ፈረንሳይ ብሄራዊ ቡድን ጋር ሲገኝ በልምምድ ወቅት ያጋጠመውን ጉዳት ተከትሎ ከ ስምንት እስከ አስር ሳምንታት እንደሚርቅ ተገልጿል ።

• አሰልጣኛቸውን ያሰናበቱት አስቶን ቪላዎች ስቴቨን ጄራርድን በቀጣዮቹ አርባ ስምንት ሰዓታት የክለቡ አሰልጣኝ አድርገው እንደሚሾሙ ይጠበቃል ።

• በርናርዶ ሲልቫ ባጋጠመው ጉዳት ሀገሩ ፖርቹጋል ከ አየርላንድ ጋር በምታደርገው የ አለም ዋንጫ ማጣርያ ጨዋታ እንደማይሰለፍ ተገልጿል ።

• ሊዮኔል ሜሲ ካጋጠመው መጠነኛ ጉዳት በማገገም ከ ሀገሩ አርጀንቲና ጋር ልምምድ መስራት ጀምሯል ።

Leave a Comment

Related Posts

en_USEnglish