Home Entertainment News ከጄፍ ቤዞስ ጋር ለሚደረገው የጠፈር በረራ አንድ ግለሰብ በ28 ሚሊዮን ዶላር ጨረታውን አሸነፈ

ከጄፍ ቤዞስ ጋር ለሚደረገው የጠፈር በረራ አንድ ግለሰብ በ28 ሚሊዮን ዶላር ጨረታውን አሸነፈ

by sam

የአማዞኑ መስራች ጄፍ ቤዞስ ወደ ጠፈር በሚያደርጉት ጉዞ ለመብረር አንድ ግለሰብ 28 ሚሊዮን ዶላር በመክፈል የጉዞውን ጨረታ ማሸነፋቸው ተሰምቷል።

በያዝነው ሳምንት ቅዳሜ በነበረው የቢሊየነሩ ብሉ ኦሪጅን ኩባንያ አማካኝነት በተደረገው ጨረታ ነው የጠፈር በረራው አሸናፊ መሆናቸው የታወቁት።

የግለሰቡ ማንነት እስካሁን ባይታወቅም በሚቀጥሉት ሳምንታት ይፋ እንደሚሆን ተነግሯል።

ጨረታው ከ140 በላይ አገራት ዜጎች የተሳፉበት ነው ተብሏል።

በሐምሌ አጋማሽ ሊደረግ በተካሄደው በዚህ የጠፈር በረራ ላይ የጄፍ ቤዞስ ወንድም ማርክና ስማቸው ያልተጠቀሰ የጠፈር ቱሪስት ተሳታፊ ይሆናሉ ተብሏል።

Leave a Comment

Related Posts

en_USEnglish