Home Entertainment News የአማዞን መስራች ጄፍ ቤዞስ የቀድሞ ባለቤት የነበረችው ቢሊየነሯ ማኬንዚ ስኮት 2.7 ቢሊየን ዶላር ለተለያዩ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ለገሰች።

የአማዞን መስራች ጄፍ ቤዞስ የቀድሞ ባለቤት የነበረችው ቢሊየነሯ ማኬንዚ ስኮት 2.7 ቢሊየን ዶላር ለተለያዩ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ለገሰች።

by sam

ማኬንዚ ስኮት የሰጠችውን ከፍተኛ መጠን ያለው የልገሳ ገንዘብን በተመለከተ በጻፈችው ጽሁፍ ላይ እንዳለችው ገንዘቡን “ከዚህ ቀደም ችላ ለተባሉና ከሚገባቸው በታች የገንዘብ ድጋፍ ላገኙ” የበጎ አድራጎት ድርጅቶች የተበረከተ።

በዚህም መሠረት ወደ ሦስት ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋውን ገንዘብ በዘር መካከል ባለው ያለመመጣጠን ዙሪያ፣ በጥበባትና በትምህርት ዙሪያ ለሚሰሩ 286 ድርጅቶች የተበረከተ ነው።

ማኬንዚ ስኮት በዓለማችን ላይ እጅጉን ሀብታም ከሆኑ ሴቶች መካከል የምትጠቀስ ናት።

አብዛኛው ሀብቷ የመጣው በአሁኑ ጊዜ የዓለማችን ቀዳሚ ባለጸጋ ከሆነው ጄፍ ቤዞስ ጋር የነበራት ጋብቻ ከሁለት ዓመት በፊት በፍቺ ሲቋጭ ከጋራ ሀብታቸው የተካፈለችው ገንዘብ ነው።

Leave a Comment

Related Posts

en_USEnglish