Home Sport News ፖል ፖግባ ከቅጣት አመልጧል

ፖል ፖግባ ከቅጣት አመልጧል

by sam

ትላንት ምሽት በ ዩሮ 2020 ላይ የ ‹COVID-19› ፕሮቶኮል አላከበረም በሚል ፖል ፖግባ ቅጣት እንደሚጠብቀው ቢታመንም ከቅጣት ነፃ መሆኑ ተረጋግጧል ፡፡

ፖግባ በ አሊያንዝ አሬና ፈረንሳይ ጀርመንን 1-0 ስታሸንፍ የጨዋታው ኮከብ ተብሎ መሰየሙ ሲታወስ ከጨዋታው መጠናቀቅ በኋላ ወደ ደጋፊዎች በመሄድ ማልያውን ለተመልካች በመስጠት ፎቶ መነሳቱ የቅጣቱ ምክንያት ነበር ።

ፖግባ ቅጣት ሊያጋጥመው ይችላል የሚሉ በርካታ አስተያየቶች ቢነገሩም በ 26 ዓመቱ አማካይ ላይ ምንም ዓይነት ቅጣት እንደማይተላለፍ የ አውሮፓ እግር ኳስ ማህበር አሳውቋል ፡

Leave a Comment

Related Posts

en_USEnglish