Home Entertainment News አዲስ አይነት የሰው ዝርያ ቅሪተ አካል በእስራኤል ተገኘ

አዲስ አይነት የሰው ዝርያ ቅሪተ አካል በእስራኤል ተገኘ

by sam

በእስራኤል ያሉ ተመራማሪዎች ከ 100 ሺህ ዓመታት በፊት ይኖር የነበረ እስካሁን የማይታወቅ የጥንት ሰው ዝርያ ቅሪት አገኙ።

በራምላ ከተማ አቅራቢያ የተገኙት ቅሪቶች እጅግ ጥንታዊ የሆነው አንድ የሰው ልጅ ቡድን የመጨረሻ በሕይወት የተረፉ ሰዎችን ይወክላሉ ሲሉ ተመራማሪዎቹ ተናግረዋል።

ቅሪቶቹ ከ140,000 እስከ 120,000 ዓመታት በፊት የኖሩ አንድ ሰው ከፊል የራስ ቅል እና መንጋጋን ይዘዋል። የግኝቱ ዝርዝር በሳይንስ መጽሔት ውስጥ ታትሞ ተሰራጭቷል።

የተመራማሪ ቡድነ አባላቱ ግለሰቡ በመቶ ሺዎች ከሚቆጠሩ ዓመታት በፊት ከነበሩ ቀደምት ዝርያዎች የተገኘ እና ከአካባቢው ተነስቶ አውሮፓ ውስጥ ለሚገኙ ኒያንደርታሎች እና በእስያ ለሚገኙ ተመሳሳይ አቻዎቻቸው መነሻ ሊሆኑ ከሚችሉ ቀደምት ዝርያዎች መካከል ነው ብለው ያምናሉ።

የሳይንስ ሊቃውንቱ አዲስ ያገኙትን ዝርያ “የነሸር ራምላ ሆሞ ዓይነት” ሲሉም ሰይመውታል። የቴል አቪቭ ዩኒቨርሲቲው ዶ/ር ሂላ ሜይ ግኝቱ የሰው ልጅ የዝግመተ ለውጥ ታሪክን በተለይም የኒያንደርታል ታሪክን ይለውጣል።

Leave a Comment

Related Posts

en_USEnglish