Home Entertainment News የጎረቤቶች አለመስማማት አንድን ዛፍ በከፊል እንዲቆረጥ አደረገ

የጎረቤቶች አለመስማማት አንድን ዛፍ በከፊል እንዲቆረጥ አደረገ

by sam

ዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ በመግቢያ መንገድ ላይ ባለ ዛፍ ምክንያት በጎረቤታሞች መካከል በተፈጠረ አለመግባባት አንድ ዛፍ በግማሽ እንዲቆረጥ ተደረገ።

በዎተርቶርፕ ሼፊልድ ነዋሪ የሆኑት የ56 ዓመቱ ባሐራት ሚስትሪ እንደሚሉት ጎረቤታቸው ከእርግቦች ጎጆ በሚወጣ ቆሻሻ ምክንያት ቅሬታ ማቅረባቸውን ተናግረዋል።

የዛፎችን ቆራጭ ከመጠራቱ በፊት ሁለቱም ጎረቤታሞች “በሠላማዊ መንገድ” መፍትሔ ላይ ለመድረስ ቢሞክሩም ሌላኛው ነዋሪ ዛፍ ቆራጭ ጠርተዋል ብለዋል።

የሚስትሪ ጎረቤት ባለመገኘቱ አስተያየቱን ማካተት አልተቻለም።

ጎረቤታቸው ባልና ሚስቶች መጋቢት መጀመሪያ ላይ ዛፉ እንዲቆረጥ ጠይቀው እንደነበር ሚስትሪ ተናግረዋል።

በመቀጠልም ዛፉን ለመከርከም ወይንም ወፎቹ ጎጆዋቸውን እንዳይቀልሱ ለመከላከል መረቦችን ለማልበስ “በርካታ ውይይቶች” ተካሂዷል።

ሚስትሪ ለዛፍ ባለሙያዎች እና አትክልተኞች ጥያቄዎችን ያቀረቡ ቢሆንም የ28 ዓመቱ ጎረቤታቸው የራሱን ዛፈፍ ቆራጭ በመጥራት እርምጃ ወስዷል።

“መጀመሪያ ሲያደርገው እኛ እንደተቆጣን መገመት ትችላላችሁ” ብለዋል።

“በግልጽ ለማየት እንደሚቻለው ከሁለት ቀናት በኋላ ትንሽ ተረጋጋን።”

የዛፉ ፎቶዎች በበይነ መረብ ከተለቀቁና ብዙዎች ከተጋሯቸው በኋላ ዛፉ የቱሪስት መስህብ ሲሆን ብዙዎች ሊጎበኙት ወደ አካባቢው አቅንተዋል።

ሌላኛው ጎረቤታቸው ብራያን ፓርክስ ጉዳዩ “በትንሹ እየተጓዘ” እንደነበረ ገልፀው “ለሁለቱም ማዘን አለባችሁ” ብለዋል።

“በጣም አስከፊ ይመስላል። አሁን ተጠናቅቋል። መቀልበስ አይችሉም። ሁለቱ ጎረቤታሞች ክፉኛ ነበር የተቃቃሩት፤ ጦርነት ማለት ይቻላል” ብለዋል ጎረቤታሞቹን አለምግባባት ሲገልጹ።

እዚያው ሰፈር የምትኖረው አን ዊልስ በበኩሏ ጎረቤታሞቹ ከዚህ ቀደም የልጆችን ድግስ በአንድነት እንዳዘጋጁ ተናግራለች።

“እስከማውቀው ድረስ በጥሩ ሁኔታ አብረው እንደኖሩነው። እኛ በመቶዎች የሚቆጠሩ ብዙ ርግቦችን አግኝተናል። በአንድ አገር ውስጥ ስለምንኖር እነዚህን ነገሮች መቀበል ነበረባቸው” ብላለች።

ዛፉ በሳይደርቅ መቆየት ካልቻለ መቆረጥ ሊኖርበት እንደሚችል ሚስትሪ ተናግረው ሆኖም የበለጠ ሊቆረጥ ወይም ሊስተካከል ይችላል የሚል እምነት አላቸው።

ባለቤታቸው ደግሞ ነገሩ “ወደዚህ ደረጃ በመድረሱ በእውነት በጣም አዝናለሁ” ብለዋል።

Leave a Comment

Related Posts

en_USEnglish