Home Entertainment News አሜሪካዊው በእንቅስቃሴ ላይ ከነበረ አውሮፕላን ዘሎ ወረደ

አሜሪካዊው በእንቅስቃሴ ላይ ከነበረ አውሮፕላን ዘሎ ወረደ

by sam

በሎስ አንጀለስ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ አንድ መንገደኛ ከሚንቀሳቀስ አውሮፕላን ላይ ዘሎ ወርዷል።

መንገደኛው የአብራሪዎቹን በር ለመክፈት ከሞከረ በኋላም ነው ዘሎ የወረደው ተብሏል።

ስሙ ያልተጠቀሰው ይህ መንገደኛ በአውሮፕላኑ የአደጋ ጊዜ መውጫ በርንም ከፍቶ እንደዘለለ የአሜሪካ አቪየሽን አስተዳደር አስታውቋል።

ወዲያውኑም ግለሰቡም በቁጥጥር ስር የዋለ ሲሆን የደረሰበት አደጋ ባይገለፅም ወደ ሆስፒታል መወሰዱ ተነግሯል።

የበረራ ሰራተኞች እንደተናገሩት መንገደኛው ከመቀመጫው ተነስቶ ወደ አብራሪዎቹ ክፍል መጠጋቱን ነው።

ከዚያም የአብራሪዎቹን በር በኃይል ካንኳኳ በኋላ በአደጋ ጊዜ መውጫ በሩ ዘሎ እንደወረደ ኤንቢኤስ ዘግቧል።

ኤምብሬር 175 የተሰኘው ይህ አውሮፕላን ወደ መነሻው እንደተመለሰም ተገልጿል።

Leave a Comment

Related Posts

en_USEnglish